
በበጀት ዓምእቱ የኑሮ ውድነት ቅነሳን በተመለከተ
በከተማዋ አምራቾች ምርታቸውን በቀጥታ በገበያ በማዕከላት እንዲያቀርቡ በተፈጠረው እደል 3.5 ሚሊዮን ኩንታል ምርት እንዲቀርብ ተደርጓል።
የቅዳሜና እሁድ የገበያ ቦታዎችን በማስፋት ከ193 ወደ 219 በማሳደግ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ እየቀረበ ይገኛል፡፡
በድጎማ ከሚቀርቡ ምርቶች የስኳር ምርት 305,295 ኩንታል፤ የምግብ ዘይት 4,382,179 ሊትር በትስስር ማሰራጨት ተችሏል።
በትራንስፖርት፣በጤና መድን፣ በዳቦ አቅርቦት፣ በምገባና በምርት አቅርቦት ከ14 ቢሊዬን ብር በላይ በመደጐም የነዋሪዎቻችን የኑሮ ጫናን የማቅለል ስራ ተሰርቷል፡፡
የዳቦ አቅርቦትን ለመጨመር በመንግስትና በግል ባለሀብቶች የጋራ ጥምረት በተሰራው ሥራ የሸገር ዳቦና ብረሃን ዳቦ ፋብሪካ ውደ ስራ በማስገባት፤በአጠቃላይ በ26 ዳቦ ፋብሪካዎች በሚሊዮኖች ዳቦ በማምረት የነዋሪውን ኑሮ ለመደገፍ ጥረት ተደርጓል።
በ26 የምገባ ማእከልላት በቀን አንድ ጊዜ ምግብ ማግኘት ችግር ላለባቸው 36ሺ ሰዎችን በምገባ ፕሮግራም ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.