"ከተማ አስተዳደሩ ባለፉት ሁለት ዓመታት ከአገል...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

"ከተማ አስተዳደሩ ባለፉት ሁለት ዓመታት ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር ያሉ ክፍተቶችን ለማረም ልዩ ትኩረት ሰጥቶት በመሰራቱ በርካታ ለዉጦችን እያመጣ ይገኛል፡፡"ዶ/ር ጀማሉ ጀምበር

ይህን ያሉት በ3ኛዉ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባዔ ላይ ለምክር ቤት አባላት በሰጡት ምላሽ ነዉ፡፡

በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰዉ ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ጀማሉ ጀምበር እንደገለፁት አገልግሎት ሰጩ ተቋማት ለአገልጋይም ሆነ ለተገልጋይ ምቹ እንዲሆኑ ከማድረግ አንፃር ለአገልግሎት አሰጣጥ ማነቆ የሆኑ አሰራሮችን፤አደረጃጀቶችን እና ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ቀልጣፋ፤ፍትሃዊ እና ተደራሽ ስራዎች ተሰርተዋል ብለዋል፡፡

በርካታ ተቋማት ከመደበኛ ስራቸዉ ወጪ ቅዳሜ እና እሁድን ጨምረዉ አገልግሎት እየሰጡ በመሆኑ የተጀመዉ አገልግሎት በተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አንስተዉ ከተማ አስተዳደሩ ባለፉት ሁለት ዓመታት ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር ያሉ ክፍተቶችን ለማረም ልዩ ትኩረት ሰጥቶት በመሰራቱ በርካታ ለዉጦችን እያመጣ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

አገልግሎት አሰጣጡን ይበልጥ ዲጂታላይዝ በማድረግ ከአገልግሎት አሰጣጠጥ፤ከፍትሃዊነት፤ከሌብነትና ከብልሹ አሰራር የሚነሱ ችግሮችን ለመቅረፍ በትኩረት እየተሰራ የሚገኝ መሆኑን ጠቅሰዉ ስራዉ የሁሉንም እርብርብ ይጠይቃል  ሲሉ ዶ/ር ጀማሉ ጀምበር ተናግረዋል፡፡፡

ከበሲቪል ምዝገባና በነዋሪነተር አገልግሎት የሲስተም መቆራረጥ ፤ከመሬት ጋርም የካርታ ህትመት ጨምሮ ያለዉን ችግር ለመፍታት ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝም ገልፀዋል፡፡
 
እንደሃገርም ሆነ እንደከተማም በአቅጣጫ የተሰጠዉን የአገልግሎት አሰጣጣችን ዲጂታል እንዲሆን መሶብ የዲጂታል አንድ ማእከል ለማስጀመር በእንቅስቃሴ ላይ መሆኑን ጠቁመዉ የአንድ መሶብ አገልግሎት በሚጀመርበት ወቅት አገልግሎት አሰጣጡአሁን ካለበት ቀልጣፋ፤ፍትሃዊና ተደራሽ ይሆናል ብለዋል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.