በመዲናዋ የወንዝ ዳርቻሞችን በማልማት የጎርፍ አ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በመዲናዋ የወንዝ ዳርቻሞችን በማልማት የጎርፍ አደጋ ተጋላጭነትን መቀነስ መቻሉን ::በምክትል ከንቲባ ማእከል የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሲታ ተናገሩ

የወንዝ ዳርቻሞችን በማልማትና በማጽዳት በወንዝ ዳርቻ ዙርያ የሚኖሩ ከ13 ሽህ በላይ ዜጎችን ከጎርፍ አደጋ ተጋላጭነት መታደርግ መቻሉን በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሲታ ተናገሩ፡፡ 

በ3ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ  በሰጡት ማብራሪያ ከ247 በላይ ለጎርፍ ተጋላጭ የሆኑ ቦታዎች መለየታቸውን ሙሉ ለሙሉ አደጋውን አለማስቀረት በትኩረት እየተሰራ እንደሆነም ኢንጂነር ወንድሙ ሲታ አስረድተዋል፡፡ 
 
እንዲሁም በያዝነው ክረምት በደረቅ ቆሻሻዎች፣በፕላስቲክ እና በኮንስትርክሽን ተረፈ ምርቶች ሊደርስ የሚችልን አደጋ ለመቀነስም ከተቋማት ጋር በቅንጅት የማጽዳት ስራ እየተሰራ እንደሆነም ተናግረዋል::


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.