በኮሪደር ልማት ተነሺ የሆኑ የልደታ ክፈለ ከተ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በኮሪደር ልማት ተነሺ የሆኑ የልደታ ክፈለ ከተማ ነዋሪዎች ዛሬ የኮንዶሚኒየም ቤት እጣ አውጥተዋል:: በልደታ ክፍለ ከተማ በኮሪደር ልማት ተነሺ የሆኑ 81 የቀበሌ ቤት ነዋሪዎች በዛሬው እለት የኮንዶሚኒየም ቤት እጣ አውጥተዋል::

 በልደታ ክፍለ ከተማ በኮሪደር ልማት ተነሺ የሆኑ 81 የቀበሌ ቤት ነዋሪዎች በዛሬው እለት የኮንዶሚኒየም ቤት እጣ አውጥተዋል::

 በዛሬው እለት በኮሪደር ልማት የሚነሱ ነዋሪዎች በራሳቸዉ ምርጫ _የኮንዶሚኒየም ቤት የመረጡ የወረዳ 4 እና ወረዳ 10 አካባቢ ነዋሪዎች በዛሬው እለት እጣ እንዲያወጡ ተደርጓል።

የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሰኢድ አሊ የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ምክትል ዳይሬክተር ኢንጂነር ቶማስ ደበሌን ጨምሮ የከተማ፣ የክ/ከተማና የወረዳ የተግባሩ አስተባባሪ አመራሮች ተገኝተው ለነዋሪው እጣ በማስወጣት ቤት አስተላልፈዋል፡፡

ከተማዋ የሀገራችን ዋና መቀመጫ፣ የአፍሪካ መዲናና አለም አቀፍ ዲፕሎማት መቀመጫ እንደመሆኗ ለህዝቧ፣ ለጎብኝዎቿ አቀባበል የምትመች ልትሆን የሚገባ በመሆኑ ከተማ አስተዳደሩ የልማት ስራዎችን ነድፎ እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

አቶ ሰኢድ አያይዘውም በልደታ ክ/ከተማ ከሜክሲኮ ሳርቤትና ጎተራ አካባቢ ለተነሱ ነዋሪዎች አዲስ አባባን እንደ ስሟ ውብ ለማድረግ የልማት ስራ ለመስራት እየተንቀሳቀስን ነው ብለው ልማቱ እንዲሳካ የነዋሪዎቿም ፍላጎት ከፍተኛ ነው ሲሉ ጠቅሰዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ምክትል ዳይሬክተር ኢንጂነር ቶማስ ደበሌ ለሰው ልጆች “መጠለያ ሁሉ ነገራቸው” እንደሆነ ጠቅሰው ልማቱ እንዲካሄድ ቀድሞ መስተካከል የሚገባቸውን ለልማት ተነሺዎች ቤት በማሟላት ለእጣ ማዘጋጀታቸውን ተናግረዋል፡፡

የእጣ አወጣጥ ሂደቱ ላይ ነዋሪው የሚያነሳው ጥያቄና ቅሬታ ካለ ከክ/ከተማ ቤቶች አስተዳደር ጀምሮ እስከ ከተማ ቤቶች ኮርፖሬሽን በአሰራር መሰረት ለመመለስ ዝግጁ መሆናቸውን በመርሀ ግብሩ ላይ ተመላክቷል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.