በካፒታል ፕሮጀክት ተግባራዊ ያደረግናቸው የልማት...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በካፒታል ፕሮጀክት ተግባራዊ ያደረግናቸው የልማት ስራዎች ዘላቂ ልማትን የሚያረጋግጡ ፤የገቢ ምጭን የሚያሳድጉና ወጪ በሚቀንሱ ናቸው::የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ እና የኢዱስትሪ ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ ዣንጥራር ዓባይ

በካፒታል ፕሮጀክት ተግባራዊ ያደረግናቸው የልማት ስራዎች ዘላቂ ልማትን የሚያረጋግጡ ፤የገቢ ምጭን የሚያሳድጉና ወጪ በሚቀንሱ ሁኔታ የተገነቡት ከ15.960 በላይ ፕሮጀክቶትን ከህብረተሰቡ ትብብርና፤ በባለሀብቶች ድጋፍና በመንግስት ወጪ ማሳካት የተቻለነው ብለዋል፡፡ 

ከ2010 ጀምሮ እያደገ የመጣውን የከተማዋን የገቢ አሰባሰብ ስርዓትን በማሳድ፤የግንዛቤ ስራ በመስራትና አዳድስ የገቢ መሰረት በማስፋት ገቢን ማሳደግ ተችሏል፡፡

የሴቶችን የአመራር ሰጪነትና ተጠቃሚነትን ለማሳደግ በተሰራው ስራ በአመራር ሰጪነት ከ33% በላይ ማሳደግ የተቻለ ሲሆን፤ በማህበራዊ ፤ በኢኮኖሚያዊና በፖተሊካዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነታቸውን ይበልጥ ለማሳደግ የከተማ አስተዳደሩ በትክረት እየስራ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡ 
 
የትራንስፖርት መሰረተ ልማትን በማስፋት በተለይም በከተማዋ በስፋት የሚስተዋለውን የተራፊክ ማኔጅመንት ላይ የሚነሱ ክፍተቶችንና የፓርክንግ አገልግሎት ችግር ለመቅረፍ በኮሪደር ልማት ስራችን የትራንስፖርት ስርዓቱን ለማዘመን በርካታ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ፡፡

ማህበራት ላይ የሚነሱ ችግሮችን በመቅረፍ፤ ሪፎርም በማድረግ፤ በማዘመንና አቅማቸውን በማሳደግ ወደ ኢንቫስትመንት እንዲደገቡ ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ ነው፡፡

ከንግድ ስርዓት ጋር በተያያዘ ሰፋፊ ስራዎችን አቅርቦትን በማይጎዳ መልኩ የቁጥጥር ስርዓቱን በማስፋት ከ36.000 በላይ ህገ-ወጦች ላይ እርምጃ በመውሰድ ወደ መደበኛ ስርዓት እንዲገቡ ተደርጓል፡፡ 

የፍሳሽ ማስወገድ ስርዓት በማዘመን ወደ ወንዞች የሚፈሱ ፍሳሾችን ለማስወገድና ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት እንዲያስችል በኮሪደር ልማቱ ሰፋፊ ስራዎችን እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.