
ህብረተሰቡ ጉቦ መስጠት የሚጸየፍና ለመብቱ የሚታገል መሆን አለበት፡፡ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ሌብነትና ብልሹ አሰራርን ከማስተካከል አንጻር ለውጡ ከህብረተሰባችን መጀመር አለበት፡፡
እንደ መንግስት ሲቪል ሰርቪሱን ሪፎርም ለማድረግና ተቋሞቻችን ለማጠናከር ከፍተኛ ጥረቶች እያደረግን ነው፡፡ ከዚህ አንጻር አገልግሎቶች መንግስት በተቀያየረ ቁጥር የሚቀያየር እንዳይሆንና አገልግሎት አሰጣጡ መሰረት እንዲይዝ ለማድረግና በሚሰራው ስራ ላይ በቂ እውቀት ያለው ሲቪል ሰርቫት ለመፍጠር በትኩረት እየሰራን ነው፡፡
ይሄን ለማሳካት ባደረግነው ጥረት ውስጥ የተለያዩ ተግዳሮቶች ማጋጠማቸውም የሚታወስ ነው፡፡አሁንም ቢሆን ህዝቡ በመታገልና የአፈጻጸም ችግር ያለባቸውን በማጋለጥ ለአገልግሎት መሻሻል የበኩሉን ድርሻ በመወጣት ለውጡን ማፋጠን አለበት፡፡
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/addisababacommunication
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.