93የቄራ፣ የጎተራና የሜክሲኮ አካባቢ የልማት ተ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

93የቄራ፣ የጎተራና የሜክሲኮ አካባቢ የልማት ተነሺዎች ዛሬ የኮንዶሚኒየም ቤት እጣ አውጥተዋል

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በኮሪደር ልማት ተነሺ የሆኑ 93 የቀበሌ ቤት ነዋሪዎች በዛሬው እለት የኮንዶሚኒየም ቤት እጣ አወጡ

የክፍለ ከተማው አስተዳደር ባለፈው ሳምንትም ለ86 የልማት ተነሽዎች በየካ ጣፎ ሳይትና በበረከት ሳይት የጋራ መኖሪያ(ኮንዶሚኒየም) ቤት እንዲያገኙ ማድረጉ ይታወሳል

 በዛሬው እለት በኮሪደሩ ልማቱ የሚነሱ 93 የኮንዶሚኒየም ቤት የመረጡ የቄራ፣ የጎተራና የሜክሲኮ አካባቢ ነዋሪዎች በዛሬው እለት እጣ እንዲያወጡ ተደርጓል።

በቀጣይም እጣ ባወጡበት በወታደር፣ ፋኑኤል፣ ጀሞ ጋራ ፣ የካ ጣፎ፣ ቡልቡላ፣አራብሳ ፣ፉሪ ሀና እና ጎሮ ስላሴ የጋራ መኖሪያ ቤት በግልፅ ሄደው በመጎብኘት ቁልፍ የሚረከቡ ይሆናል።

በቀጣይም ሌሎች የልማት ተነሺዎችን እንደ ምርጫቸው የማስተናገድ ስራ እንደሚሰራም ተገልጿል።

ቂርቆስ ሚዲያም ከኮሪደር ልማት ጋር ተያይዞ የሚወሰኑ ውሳኔዎችንና ያሉ መረጃዎችን በየእለቱ እየተከታተለ ለህዝቡ ተደራሽ የሚያደርግ ይሆናል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.