ዛሬ ጠዋት ከቦሌ ካርጎ እስከ አቃቂ ድልድይ በመሰራት ላይ የሚገኘውን የአረንጓዴ ልማት ስራ ተዘዋውረን ጎብኝተናል።
ከተማችንን ጽዱ፣ ውብ እና አረንጓዴ ለማድረግ የጀመርነው የኮሪደር ልማት አካል የሆነው ይህ የአረንጓዴ ልማት ስራ የህጻናት መጫዎቻዎችን፣ መናፈሻዎችን እንዲሁም የተለያዩ ለአካባቢው ነዋሪዎች ግልጋሎት የሚሰጡ ስራዎችን የሚያካትት፣ ከ200 ሺሕ ካሬ በላይ ሽፋን ያለው እና ከቦሌ ካርጎ እስከ አቃቂ ድልድይ ድረስ 9.5 ኪ ሜ የሚረዝም ሲሆን ስራውን በአጭር ጊዜ ውስጥ በማጠናቀቅ ለህዝብ ክፍት እናደርጋለን።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.