ከሁሉም የሃገራችን አካባቢዎች የመጡ የሁሉም ተፎካካሪ ፓርቲ ተወካዮች የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎብኝተዋል::
ከጉብኝቱ በኃላም በአዲስ አበባ የተጀመረው የልማት ኮሪደር አላማ እና አሁን ያለበት ደረጃ ለተፎካካሪ ፓርቲ ተወካዮቹ ማብራሪያ ተሰጥቷል::
የዓድዋ ድል መታሰቢያ ለቀጣይ ትውልድ ቋሚ ቅርስ በሚሆን መልኩ መገንባቱ እንዳስደሰታቸው ያነሱት ጎብኚዎቹ የዓድዋ ድል መታሰቢያ የጋራ ታሪካችንን በልኩ ሰንዶ የያዘ ፣ አንድነታችንን የሚያጸና ግዙፍ ፕሮጀክት መሆኑን እና የልማት ኮሪደር አላማ ከተማዋን ማስዋብ መሆኑን መረዳታቸውን ገልጸው ከልማት ተነሺዎች የሚነሳ ማንኛውንም ቅሬታ ከፍተኛ አመራሩ አዳምጦ መመለሱን አሁንም አጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል::
በጉብኝቱ ወቅት ንግግር ያደረጉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ የተፎካካሪ ፓርቲዎች ገዢው ፓርቲ የሰራቸውን የልማት ስራዎች በማየት ማመስገን እና እውነታውን መመስከር በፖለቲካ ስርዓታችን ውስጥ አዲስ ባህል በመሆኑ ይህ አዲስ አስተሳሰብ እና ተግባር ሊዳብር ይገባል ብለዋል::
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.