
ከተማችን አዲስ አበባን የሚመጥን ኮሙኒኬሽን ሥራዎች በላቀ ብቃት እንደምንገነባ አንጠራጠርም ! የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2017 በጀት ዓመት የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ተቋማት እና ክፍለ ከተሞች ዕውቅና እና ሽልማት ሰጥቷል። ቢሮችን የከተማዋን ሁሉን አቀፍ እንቅስቃሴ ለህብረተሰቡ መረጃ በፍጥነት እንዲደርስ በማድረግ በኩል ላሳየው ላቅ ያለ አፈጻጸም የተሽከርካሪ ሽልማት ተበርክቶለታል፡፡
ጠንካራ የኮሙኒኬሽን ስርዓት በመዘርጋት ህዝባችን ብቁ በከተማው ሁለንተናዊ እቅስቃሴ ተሳታፊ እንዲሆን ጥራት ያለው መረጃ በመስጠት ለከተማችን ሁለተናዊ ፈጣን እድገት አሁንም በትጋት መስራታችንን እንቀጥላለን።
"አምና በስኬት ላይ ነበርን፤ዘንድሮም በስኬት ላይ ሆነናል፤ወደፊትም በስኬት ላይ ስኬት እየተጎናፀፍን ለከተማችን ሁለተናዊ ፈጣን እድገት በመረጃው ዘርፍ መስራታችንን እንቀጥላለን፡፡
ይህ እንዲሳካ ላደረጋችሁ በየደረጃው የምትገኙ የኮሙኒኬሽን አመራሮች ፣ስራተኞች እና የማህበረሰብ አንቂዎች በሙሉ ድሉ የእናንተም ነውና በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/addisababacommunication
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.