በኮሪደር ልማት የተነሱ 356 ነዋሪዎች የጋራ መ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በኮሪደር ልማት የተነሱ 356 ነዋሪዎች የጋራ መኖሪያ ቤት እጣ አወጡ::

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በኮሪደር ልማት ለተነሱ 356 የልማት ተነሺ የጋራ መኖሪያ ቤት እጣ የማውጣት መርሀ ግብር ተካሂዷል።

በመርሀ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ምክትል ኃላፊ ኢንጂነር ቶማስ ደበሌ እና የክፍለ ከተማና ወረዳ አመራሮች ተገኝተዋል።

 

በዚህ የልማት ስራ ተነሺ ለሆኑ 356 የክፍለ ከተማው ነዋሪዎች የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የጋራ መኖሪያ ቤት እጣ የማውጣት ስነ ስርዓት አድርጓል።

በመርሀ ግብሩ ላይ ተገኝተው መልዕክታቸውን ያስተላለፉት የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብርሃኑ አበራ ሀገራዊ የልማት ተልዕኮውን ተቀብለው ፍቃደኛ በመሆን በእጣ አወጣጥ ስነ ስርዓት ለተገኙ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ምክትል ኃላፊ የሆኑት ኢንጂነር ቶማስ ደበሌ በእጣ አወጣጥ ስነስርዓቱ ላይ ተገኝተው እንደገለፁት ህብረተሰቡ ለልማት ያለውን ፍላጎት እያሳየ ያለበትና መንግስት ደግሞ ቁርጠኛ አቋም ይዞ ልማትን እየሰራ ያለበት አግባብ የሚደነቅ ነው ብለዋል።

ኢንጂነር ቶማስ አክለው እንዳሉት በዛሬው መርሀ ግብር ብቻ 356 ነዋሪዎች የጋራ መኖሪያ ቤት እጣ አውጥተው ተጠቃሚ እንደሚሆኑ አመላክተዋል።

በመርሀ ግብሩ የቤት እድለኛ የሆኑ ነዋሪዎች በበኩላቸው መንግስት እየሰራ ያለውን ልማት እንደሚደግፉና የእጣ አወጣጥ ስነ ስርዓቱም ፍትሀዊና ግልፀኝነት ያለው እንደሆነ ተናግረዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.