ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፣ ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር አባይ እንዲሁም የልማት ኮሪደሮቹን በማስተባበር ላይ የሚገኙ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የልማት ኮሪደር እና የከተማ እድሳት ስራዎችን አስጎብኝተዋል::
የምክር ቤት አባላቱ የኮሪደር ልማት ስራዎቹ ከከተማችን አልፎ አጠቃላይ የሃገራችንን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ የሚቀይር መሆኑን የተናገሩ ሲሆን ስራዎቹ የአዲስ አበባን ውበት ከፍ የሚያደርጉ እና ተወዳዳሪነቷንም የሚጨምሩ መሆናቸውን ገልጸዋል::
ለአደጋ ተጋላጭና ምቹ ባልሆኑ የመኖሪያ አካባቢ ሲኖሩ የነበሩ የከተማችን ነዋሪዎች ንጹህ እና ዘመናዊ ቤት እንዲገቡ መደረጉ እንዳስደሰታቸው የተናገሩት የምክር ቤት አባላቱ የከተማ አስተዳደሩ በዚህ ልክ ለሰው ቅድሚያ በመስጠት እየሰራ መሆኑን መመልከታቸውን ገልፀው ይህ ደግሞ አንድ ልማት ብቻ ሳይሆን በርካታ የልማት ስራዎችን አሳልጠው እየሰሩ ከመሆኑ አንጻር ትልቅ ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል::
የምክር ቤት አባላቱ የከተማ አስተዳደሩ የኮሪደር ልማት ስራዎቹ በተጀመሩት ፍጥነት በማስቀጠል ክረምቱ ሳይገባ እንዲያጠናቅቅም አሳስበዋል::
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.