.png)
የአዲስ አበባ ከተማ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ በ2017 በጀት አመት በሀገር አቀፍ ደረጃ በተደረገው ምዘና አንደኛ በመውጣት ሽልማት ተበረከተለት::
የኢፌዴሪ ኢንዱስትሪ ሚንስቴር በ2017 በጀት አመት ባደረገው የስራ አፈፃፀም ከሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ተወዳድሮ የአዲስ አበባ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ አንደኛ ወጥቷል::
በዚህም ቢሮው ከኢፌደሪ ኢንዱስትሪ ሚንስትር ሚንስቴር ክቡር አቶ መላኩ አሉበል የሜዳሊያ: የዋንጫ: የኮምፒዩተር እና የላፕቶፕ ሽልማት ተበርክቶለታል::
ሽልማቱን የተቀበሉት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሃላፊ ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ ለቢሮው አመራሮችና ሰራተኞች፣ ለክፍለ ከተማ አመራሮችና ሰራተኞች በሙሉ ምስጋና አድርሰዋል።
አቶ ጃንጥራር አክለውም: የእውቅና ሽልማቱ በ2018 የተሻለ ለመስራት የሚያነሳሳ ነው ብለዋል::
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.