በአይነቱ ልዩ የሆነዉ ከእንጦጦ እስከ አራት ኪሎ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በአይነቱ ልዩ የሆነዉ ከእንጦጦ እስከ አራት ኪሎ ፕላዛ ያለዉ የኮሪደር ልማት ከሚሰጣቸዉ ጠቀሜታዎች መካከል ምን ያህሉን ያዉቁ ይሆን?

ከቀናት በፊት ተመርቆ ለህዝብ አገልግሎት ክፍት የተደረገው  ከእንጦጦ እስከ አራት ኪሎ ፕላዛ ያለው በአይነቱ ልዩ የሆነዉ የኮሪደር ልማት ከሚሰጣቸዉ ጠቀሜታዎች መካከል ፡-

👉 በሚያካልላቸው አካባቢዎች ለሚገኙ ሁሉም የማህበረሰብ ክፍሎች የከተማውን ዕድገት የሚመጥን ከዘመናዊ ፣ ጤናማ አኗኗር እና የግብይት ስርዓት ጋር የማላመድ ተጨማሪ አቅም ይፈጥራል። 

👉 በአራዳ ክፍለ ከተማ ቅጥር ግቢ ውስጥ እየተሰናዳ የሚገኘው የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ጨምሮ ሌሎች በዚህ ኮሪደር ውስጥ የሚገኙ መንግስታዊ እና የግሉ ዘርፍ ተቋማት ለደንበኞቻቸው ለሚሰጡት አገልግሎቶች ምቹ ሁኔታዎችን ከመፍጠር አንጻር ፋይዳው የጎላ ነው። 

👉 በውስጡ አቅፎ የያዛቸው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መሰረተ ልማቶች አካታችነትንና ፍትሀዊነትን በሚገባ የሚያረጋግጡ ናቸዉ። 

👉 የአዲስ አበባን  ታሪክ ፣ ልምላሜ፣ ማራኪነት እና ጽዱነት ይበልጥ የሚያጎላ በመሆኑ የአሁኑን ብቻ ሳይሆን ቀጣይ ትውልዶችን እንደ ድልድይ የማገናኘት ሀይል አለው። 

👉 በመልክዓ ምድር አቀማመጡ፣ ታሪካዊ ስፍራዎችን አካትቶ በመያዙ፣ የሀገር ውስጥም ሆነ ዓለም አቀፍ ጎብኝዎችን ፣ ተመራማሪዎችን ፣ በመሳብ የአዲስ አበባን ቱሪዝም መዳረሻነቷን ይበልጥ ማሳደግ ያስችላል። 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.