የአዲስ አበባ አዳዲስ መልኮች እና የአዲስ አበ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የአዲስ አበባ አዳዲስ መልኮች እና የአዲስ አበባ ልጆች ዝማሬ

የደማቆች ህብር ቀለም
ሰላማዊት ውቢት ዓለም
እንደስሟ ውብ ከተማ
ምስጢራዊት ህብር ሸማ
አዲስ አበባ (2) 

የህያው የታሪክ ምስክር
የአብሮነት ልዩ ምድር
የባህል ደሴት መዳረሻ
የጥቁር ህዝቦች መካሻ
የዲፕሎማሲ ማዕከላችን* 
ዓለምአቀፍ መዲናችን* 
እናት ነሽ ለዘመኑ ከተሞቻችን*
ጌጣችን ነሽ ዕንቁ ፈርጣችን* 

አዲስ አበባ 

መአዛዋ ልዩ አደስ
የአፍሪካ ግርማ ሞገስ
ስሟ መኩሪያ የሚያድስ
አበባዋ ዘወትር አዲስ 

ባንድ ማደሪያ የጋራ ቤት
የብዝሃነት፣ የአብሮነት
የሰው ተኮር ልማት*
የሰላማዊ ህይወት*
የብልጽግና መሠረት*
ማማችን ነሽ የኢትዮጵያዊነት*
የአንድነት ውብ ቀለበት
ቃል ማሰሪያ ልዩ ድምቀት 

ስመ ቃሉ ልዩ ፊደል
በወርቀዘብ የሚፈተል
ድንቅ ካባ ሽልማቱ
ሁሉ ልጇ ሁሉ ቤቱ 

ሳንባችን ነች መተንፈሻ
የሁላችን መናገሻ
ከፈጣሪ የተሰጠች
አዲስ ሁሌ ቤታችን ነች 

የማትቆም ተሻጋሪ
ኮከባችን ሁሌም አብሪ
የሁላችን ልዩ አንባ
አዲስ አዲስ አዲስ አባ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.