
“ቸር ልብ ያላቸው እልፍ ዜጎች አሉን” ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ከዲያስፓራ እስከ ሀገር ቤት ካላቸው የሚያካፍሉ፣ ከጎዶሎአቸው የሚሰጡ ፣ በመስጠት ውስጥ ያለን በረከት የተረዱ ፣ ለሀገሬ ምን አደረኩላት የሚሉ፣ ቸር፣ ሀብታም ልብ ያላቸዉ እልፍ ወንድም እህቶች አሉን ።
ዛሬም በሀገረ አሜሪካ ኮሎራዶ ግዛት የሚገኘው “ሄኖክ አርጋው ፋውንዴሽን” ዋጋቸው ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ 133 አይነት የተለያዩ የህክምና መገልገያ መሳሪያዎችን እና የህክምና ግብአቶችን አበርክቶልናል ።
መሳሪያዎቹ ለኩላሊት፣ ለተኝቶ ታካሚዎች፣ ለፅኑ እና መደበኛ ሕሙማን ህክምና ግልጋሎት የሚያግዙ ናቸው።
ሄኖክ አርጋው ፋውንዴሽንን በከተማ አስተዳደሩ፣ በተጠቃሚው ማህበረሰብ እና በራሴ ስም እጅግ አድርጌ እያመሰገንኩ፤ ድጋፉ ለታለመለት ዓላማ እንዲውልም ለአስተዳደሩ የጤና ቢሮ አስረክበናል።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.