
ዛሬ የ90 ቀን የሁለት ወር ሥራ አፈፃፀም ገምግመናል::
የአገልግሎት አሰጣጥ ማዘመን እና የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ የሚቀርቡ ግብአቶች አቅርቦትን ፣ የገበያ ማረጋጋት ፣የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት፣ የሥራ ዕድል ፈጠራ ፣ የፕሮጀክቶች ግንባታ፣ የገቢ አፍፃፀም እና ለኮንፍረንስ የቱሪዝምን ምቹ ሁኔታ መፍጠር በትኩረት ገምግመናል።
በዚህም የሁለቱ ወር ስራ አፍፃፀም ውጤታማ እንደነበረም በርካታ ማሳያዎች ቀርበዋል ።በተለይ ከኑሮ ውድነት ጋር ተያይዞ ምርቶች በስፋት ወደ ከተማው መግባታቸው ፣ የገቢ አፈፃፀም፣ የክረምት በጐ ፍቃድ አገልግሎት፣ የስራ እድል ፈጠራ እና የፕሮጀክቶች አፈፃፀም የተሻሉ እንደነበራቸው አይተናል።
በሌላ በኩል ደግሞ መሻሻል የሚገባቸው እና በክፍታት የታዩትን በፍጥነት እንዲታረም አቅጣጫ አስቀምጠናል።ከቀጣዩ ሳምንት ጀምሮ የሚከናወኑት 2ተኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ እንዲሁም የካሪቢያን መሪዎች ታላላቅ ስብስባ እና ጉባኤን በፍጹም ፀጥታ፣ በትሁት ኢትዮጵያዊ መስተንግዶ ተቀብለን ለማስተናገድ ከወትሮው የተለያ ርብርብ እንድናደርግ ፤ ሁሉም የከተማው አመራር በትኩረት እንዲሰራ ተግባብተናል::
ማህበረሰባችንም ለእንግዶቻችን ኢትዮጵያዊ ጨዋነትን በተግባር እንድናስይ ስል በአክብሮት እጠይቃለሁ::
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ !
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/addisababacommunication
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.