ዛሬ በመንግስትና የግል ዘርፍ አጋርነት መርሃግብ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ዛሬ በመንግስትና የግል ዘርፍ አጋርነት መርሃግብር የሚገነቡ የ60 ሺህ መኖሪያ ቤቶች ግንባታን አስጀምረናል። ውጣ ውረዶች ያላስቆሙት የለውጡ ፍሬያማ ጉዞ ፣ ቃል በገባነው ልክ በስኬት ታጅቦ ቀጥሏል።

ዛሬ አስተዳደራችን ባዘጋጀው 558 ሄክታር መሬት ላይ ያስጀመርነው የ60ሺህ መኖሪያ ቤቶች እና ተያያዥ መሰረተ ልማቶች ግንባታ የአንድ መካከለኛ ከተማ ግንባታ የሚያክል ነው።

የ60ሺህ መኖሪያ ቤቶች፣ ትምህርት ቤቶች፣ ዘመናዊ የንግድ ማዕከላት፣ የጤና ተቋማት፣ የመዝናኛ ስፍራዎች፣ በቂ የአረንጏዴ እና የህጻናት መጫወቻ ስፍራዎች፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎች እንዲሁም ዘመናዊ የመሰረተ ልማት የተሟላለት ከተማ አከል መንደር ሲሆን፣ ለ250 ሺሕ ነዋሪዎች የስራ እድል ይፈጥራል።

 

መንደሩ በሚገነባበት አካባቢ ያሉ ነዋሪዎችንም የልማቱ ተጠቃሚ እና አካል በማድረግ የቤት ባለቤት ከማድረግ በተጨማሪ ህይወታቸውን የሚቀይርና ተጠቃሚነታቸው የምናረጋግጥ መሆኑን ተረድተው ፈቃደኝነታቸውን ስላሳዩን ምስጋናዬን ላቀርብላቸው እወዳለሁ።

 

የእነዚህ 60 ሺሕ ቤቶችን ግንባታ በተያዘለት ጊዜ በማጠናቀቅ የከተማችን ነዋሪዎች አንገብጋቢ ጥያቄ የሆነውን የቤት አቅርቦት ችግር ለመቅረፍ የምንሰራ ሲሆን፣ የኦቪድ ግሩፕ ላደረገው ዝግጅት እና አዲስ ሃሳብ ይዞ በመምጣቱ ላመሰግነው እወዳለሁ።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.