.png)
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ 5ኛ ዓመት 2ኛ መደበኛ ስብሰባ በዛሬው እለት አካሂደናል::
ካቢኔው በዛሬው ውሎው በቀረቡ ሁለት ዋና ዋና አጀንዳዎች ላይ ውይይት በማድረግ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
በዚህ መሰረት፡-
1ኛ :-በኮሪደር እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ውስጥ የመንግስትና የግል አጋርነት ጽ /ቤት የተፈረመውን ስምምነት ለሚለሙ 30 ፕሮጀክቶች ከ733 ቢሊዬን ብር በላይ ወጪ የሚጠይቅ እና 37 አልሚዎችን የሚያካትት በመሆኑ ፤ ልማቱን ዉጤታማ ለማድረግ ካቢኔዉ መርምሮ እንዲያፀድቅ የቀረበለት አጀንዳ በመወያየት ፣ካላቸው ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ፣ የሚፈጥሩት ሰፊ የስራ እድል እና ከተማን ትብብር የማልማት ትልቅ ፋይዳ እና አዲስ አሰራር በመሆኑ ከቢኔው በቀረበ የዉሳኔ ሀሳብ ላይ ውይይት በማድረግ ውሳኔ አፆድቋል፡፡
2ኛ :-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆችን የአሰልጣኞች የዝውውርና የምደባ አፈፃፀም ደንብ በተመለከተ በቴክኒክ እና ሙያ ተቋማት ጥራት ያለው ሥልጠና ለመስጠት፣ ኮሌጆቿን ውጤታማ ከማድረግ እና በተደራጀ አግባብ ለመምራት በሚያስችል መልኩ የደንቡ መውጣት እገዛው የጎላ በመሆኑ ውይይት በማድረግ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.