
"ከአንድ አመት በፊት ወደ አሶሳ መጥተን ነበር። ዛሬ በከተማዋ ያየነው ባለፈው አመት ካየነው በፍፁም ተቃራኒ ነው።
የተለወጠበት መንገድ ጥሩ ጅማሮ ነው:: የኮሪደር ሥራ ውጤቱ የሚታይ ነው።
ከአሶሳ የተወሰኑ መቶ ኪሎሜትሮች ርቀት የሚገኘውና በማሽን የታገዘ ዘመናዊ ፋብሪካ የኩርሙክ ወርቅ ፋብሪካ አስደናቂ የሥራ ውጤት ነው። በሚቀጥለው አመት በግማሽ አቅሙ ማምረት ይጀምራል። የክልሉን ሰፊ የወርቅ አቅምም ያሳያል።
ከባለፈው አመት ጉብኝታችን በኋላ ያየነው እድገት የሚበረታታ ነው። ፕሮጀክቱ ሙሉ በሙሉ በሚጠናቀቅበት ጊዜ በጎ ተጽዕኖው በመላው ክልሉ የሚታይ ይሆናል።
መሰል ፕሮጀክቶች ከሌሎች ፕሮጀክቶች ጋር ተደምረው የሀገራዊ ብልጽግናችን መገንቢያ ጡቦች ናቸው። ማዕድን በብዝኃዘርፍ የልማት ምልከታችን አንዱ ቁልፍ ዘርፍ ሆኖ ይቀጥላል። የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልልም ለዚህ ርዕይ መሳካት ዐቢይ ሚና ያለው መሆኑን እያስመሰከረ ይገኛል"።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓብይ አህመድ
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/addisababacommunication
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.