.png)
“ ከተማ አስተዳደሩ የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት በቀጥታ 14.5 ቢሊዮን ብር ድጎማ አድርጓል
ህገወጥ ንግድን በመቆጣጠር እና ገበያን በማረጋጋት አዲሱን ዓመት ለመቀበል ተዘጋጅተናል”
የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ፤
የገበያ ማረጋጋት፣ ህገወጥ ንግድ ቁጥጥር እና የኢትዮጵያ አዲስ አበባ ታምርት ንቅናቄ ግብረ ሀይል ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ጃንጥራር አባይ በዛሬው እለት ለመገናኛ ብዙሀን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
ከተማ አስተዳደሩ የኑሮ ጫናን ለማቃለል ለአቅርቦት ምቹ ሁኔታ በመፍጠርና ተቋማዊ አደረጃጀት በመዘርጋት የገበያ ማዕከላት በመገንባት: የቅዳሜና እሁድ ገበያ ቦታ በማመቻቸት ምርት በማህበራትና በአምራቾች በቀጥታ እየቀረበ መሆኑን ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር አባይ በመግለጫቸው ገልፀዋል::
ምክትል ከንቲባዉ በተጨማሪም : ከተማ አስተዳደሩ የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት በቀጥታ 14.5 ቢሊዮን ብር የድጎማ በጀት በመመደብ ለተማሪዎች ምገባና ዩኒፎርም: ለትራንስፖርት አቅርቦት: ለጤና መድን: ለመንግስት ሰራተኞች የካፍቴሪያ ድጎማ ለማህበራትና ንግድ ስራዎች ሪቮልቪንግ ፈንድ በማቅረቡ የገበያ መረጋጋት ተፈጥሯል ብለዋል::
ገበያ እንዲረጋጋ፣ ህገወጥ ንግድ ወደ ህጋዊ መስመር እንዲገባም ከተማ አስተዳደሩ የገበያ ማረጋጋት፣ ህገወጥ ንግድ ቁጥጥር እና የኢትዮጵያ አድስ አበባ ታምርት ንቅናቄ ግብረ ሀይል አቋቁሞ እየሰራ ይገኛል፡፡
በከተማ አስተዳደሩ መውጫና መግቢያ በሮች 5 የገበያ ማእከላት ተገንብቶ አገልግሎት መጀመራቸውን እና ከሁሉም የሀገሪቱ ክፍል የሰብል፣ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርት በማስገባት ግብይት በመፈፀም አምራቹንና ሸማቹን በቀጥታ በማገናኘትና ደላላን በመቀነስ ከፍቸኛ ሚና እያበረከተ ነው ሲሉም ምክትል ከንቲባዉ ገልጸዋል።
በአጠቃላይ የገበያ ማዕላት ገበያን በማረጋጋት፣ አምራችና ሸማች በማገናኘትና ከገበያ ዋጋ ከ15-20% ቅናሽ በማድረግ ዝቅተኛውን ማህበረሰብ ለመደገፍ ጥረት ተደረጓል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.