.png)
ብዝሀ አርበኝነትን የምናረጋግጠው በስራ እና በስራ በመሆኑ የህዝባችንን ተጠቃሚነት ለማሳደግ ርብርቡን ማጠናከር ይገባል - አቶ ሞገስ ባልቻ
የስራ ዕድል ፈጠራን ፣ የከተማ ግብርናን እንዲሁም ተረጅነትን ወደ አምራችነት ለማሸጋገር የሚደረገውን ርብርብ የሚያስተባብሩ የጋራ ግብረ ሀይል አመራሮች የ90 ቀናት የንቅናቄ ስራዎችን የ70 ቀናት አፈፃፀም ገምግመዋል።
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ በውይይቱ ላይ እንደገለፁት የተመዘገቡ ስኬቶችን በማጠናከር ጉድለቶችን ፈጥኖ በመሙላት አዲሱን ዓመት በላቀ ስኬትና ተነሳሽነት ለመቀበል ግምገማው ተጨማሪ አቅም እንደሚሆን አስረድተዋል።
የዘጠና ቀናት የንቅናቄ ስራዎች ሲጀመሩ ቆጥረን የወሰድናቸውን ተግባራት ቆጥርን የምናስረክበው ጳጉሜ 5 መሆኑን መዘናጋት አይገባም ያሉት አቶ ሞገስ ሁሉንም ተግባራት በመልካም አፈፃፀም ለማጠናቀቅ በሙሉ አቅም ቅንጅታዊ ርብርብን ማጠናከር እንደሚገባ አሳስበዋል።
ብዝሀ አርበኝነት የሚረጋገጠው በስራ እና በስራ በመሆኑ የህዝባችንን ተጠቃሚነት ለማሳደግ ርብርቡን ማጠናከር እንደሚገባ የገለፁት አቶ ሞገስ ተደራራቢ ተልዕኮዎችን በብቃት በመወጣት ውጤታማነትን ማላቅ እንደሚገባ አመላክተዋል።
ምርት እና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚደረገውን እንቅስቃሴ በሁሉም መልክ ከፍ ማድረግ እንደሚገባ ያሳሰቡት አቶ ሞገስ ሁሉም አደረጃጀቶች ለከተማችን ነዋሪ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ቅንጅታዊ ስራዎችን ሊያጠናክሩ እንደሚገባም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጥራቱ በየነ በበኩላቸው በሚመዘገቡ ውጤቶች መዘናጋትን በማስወገድ የንቅናቄ ስራዎችን በጥብቅ ዲሲፕሊን መምራት እና አማራጭ ፀጋዎችን ማስፋት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
ወደ ፊት የተራመዱ ተቋማትን አርአያነት በመከተል የተጀማመሩ ስራዎችን ማጠናከር እንደሚገባ ያስረዱት አቶ ጥራቱ በከተማ ግብርና ሰፋፊ ፀጋዎችን በአግባቡ ከመጠቀም አኳያ አሁንም የሚስተዋሉ ውስንነቶችን ማረም እንደሚገባም አሳስበዋል።
ባለፉት 70 ቀናት የስራ ዕድል ፈጠራ አፈፃፀም 98 በመቶ የደረሰ ቢሆንም ዘላቂ ዕድገትን የሚያረጋግጡ ዋና ዋና ዘርፎችን አቅም በአግባቡ ከመጠቀም አኳያ ያሉትን ክፍተቶች መቅረፍ እንደሚገባ በግምገማው ተመላክቷል።
በተቋማት መካከል ያለው ሰፋ ያለ የአፈፃፀም ልዩነት ሊጠብ እንደሚገባም የተጠቆመ ሲሆን በከተማ ግብርና ነባር ኢንተርፕራይዝ ከማስቀጠል አንፃር የተስተዋሉ ጉድለቶችንም ማረም ይገባል ተብሏል።
በተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ውስጥ የነበሩ ዜጎችን የስነ ልቦና እና ልዩ ልዩ የክህሎትና የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን በመስጠት ወደ አምራችነት ለማሸጋገር የተጀመረውን ርብርብ ማጠናከር እንደሚገባም ተገልጿል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.