.png)
ለሚሰጡት አገልግሎት ጉቦ የጠየቁ አመራሮች በቁጥጥር ስር ዋሉ።
የቄራዎች ድርጅት የሚሰጠውን አገልግሎት ለማግኘት የሄዱ ተገልጋዮችን ገንዘብ የጠየቁ ሁለት ተጠርጣሪ አመራሮች ፣ 1ኛ የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰይድ እንድሪስ ከማል እና 2ኛ ምክትላቸው አቶ ዮሴፍ ድሪብሳ ማሞ ገንዘብ ካላመጣችሁ አገልግሎት አታገኙም በማለት ፤ እንግልት ሲፈጠሩ ቆይተው በደረሰ ጥቆማ በዛሬው ዕለት ከተገልጋይ ጉቦ ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ ተይዘው በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
ተገልጋዬች ተከታትለዉ ለሰጡት ጥቆማ እያመሰገንን ፣ በቀጣይም ሙስናን ለመከላከል በሚደረገው ትግል ከጎናችን በመሆን መተባበራችሁን እንድትቀጥሉ ጥሪያችንን እናቀርብለን።
በቀጣይም ህብረተሰቡ እንደዚህ አይነት የሙስና ተግባራትን ሲመለከት ለ ከንቲባ ጽ/ቤት የሙስና ወንጀል ጥቆማ ተቀባይ በመጠቆም ሙስናን የመከላከል ሚናውን በአግባቡ እንዲወጣ እናሳስባለን።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.