በመዲናዋ በ2017 በጀት ዓመት የተሻለ አፈፃፀም...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በመዲናዋ በ2017 በጀት ዓመት የተሻለ አፈፃፀም ላመጡ የኮሙኒኬሽን መዋቅሮች እውቅና ተሰጠ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ  በ2017 በጀት ዓመት የተሻለ አፈፃፀም ላመጡ ከማዕከል እስከ ወረዳ ለሚገኙ የኮሙኒኬሽን መዋቅሮች የምስጋና እና የእዉቅና ሰጥቷል፡፡

በእውቅና እና ሽልማት ሥነ-ሠርዓቱ ላይ ንግግር  ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ "ወ/ሮ እናትዓለም መለሰ  አጀንዳዎችን በመሸጥ እና የመረጃ ምንጭ በመሆን የሃሳብ ባለቤት መሆን ችለናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ባለፈው ዓመት ታማኝ የመረጃ ምንጭ መሆን ችለናል ያሉት "ወ/ሮ እናትዓለም መለሰ  በቀጣይም  ራስን በሙያዉ በማብቃትና ሁለተናዊ እዉቀት በመታጠቅ ፣ የተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮችን በመጠቀም በፈጠርነዉ የተቀናጀ የኮሙኒኬሽን ሠራዊት ከመቸዉም ጊዜ በበለጠ ተግተን  መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል።

በተለይም ጥራት ላለዉ ሚዛናዊ ፈጣንና ትክክለኛ  መረጃ ትኩረት በመስጠት የከተማዋን ፈጣን እድገት በሚመጥን ደረጃ  የመረጃ ምንጭ በመሆን የከተማችንን የልማት ስራዎችን  ተደራሽ ማድረግ የእኛ የኮሙኒኬሽን መዋቅር ቀዳሚ ተግባር መሆኑን አዉቀን  የበኩላችን ሚና ልንወጣ ይገባል ሲሉም  አሳስበዋል፡፡

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
  https://linktr.ee/addisababacommunication


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.