የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት እቅድ ላይ ዉይይት አካሔደ

ቢሮዉ ከማዕከል እስከ ወረዳ ካሉ የኮሙኒኬሽን መዋቅሮቹ ጋር በ2017 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀምና በ2018 በጀት ዓመት እቅድ ላይ ዉይይት አካሔዷል።

የኮሙኒኬሽን ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ በትግሉ ኪታባ በውይይቱ ወቅት እንደገለፁት በ2017 በጀት ዓመት መዋቅራችን በተቀናጀና በተናበበ አግባብ ከተማዋን በአጀንዳና በመልእክት በመምራት የመረጃ ምንጭ በመሆን የሃሳብ ልዕልና እና አንድነትን በህብረተሰባችን እንዲሰርፅ በማድረግ የተሳካ ስራ መስራት የተቻለ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አክለዉም በቀጣይ 2018 በጀት ዓመትም ካለፈዉ ልምድና ተሞክሮ በመዉሰድ እቅዳችንን የበለጠ ለማሳካት በተሻለ በመስፈንጠር፤ግቦቻችን ላይ በማተኮር ሁላችንም ከተማዉ የጣለብንን ኃላፊነት በየደረጃዉ መወጣት ይጠበቅብናል ብለዋል ፡፡

 የኮሙኒኬሽን ቢሮ ፅ/ቤት ኃላፊ  ወ/ሮ ነፃነት ዓለሙ በበኩላቸዉ ራሳችንን በማዘጋጅትና  በቴክኖሎጂ በማዘመን እንዲሁም በሙያችን ብቁ ሆኖ መስራት ላይ ሁሉም ትኩረት ሊሰጠዉ የሚገባ ነዉ ብለዋል፡፡
 
በተጨማሪም በተቀናጀ አግባብ የሚያጋጥሙንን ተግዳሮቶች እየፈታን ቀን ከሌት ሰርተን የመረጃ ምንጭ ሆነን የከተማችንን ገፅታ በማጉላት የመረጃ ተደራሽነታችን በማስቀጠል የተጣለብንን ትልቅ ኃላፊነት ለመወጣት የሚያስችል ቁመና ላይ ስለምንገኝ ይህን ማጠናከር እና ለዉጤት መብቃት የበጀት ዓመቱ ተግባራችን ነዉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡
 
በዉይይቱ ላይ የቢሮዉ አመራሮችና ሰራተኞች፤በከተማዋ የሚገኙ የኮሙኒኬሽን ሴክተር ተቋማት፤የክፍለ ከተማ እና የወረዳ ፅ/ቤቶች ተገኝተዋል፡፡

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
  https://linktr.ee/addisababacommunication


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.