ወደ ምግብ ዋስትና እና የግብርና ሽግግር በምናደ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ወደ ምግብ ዋስትና እና የግብርና ሽግግር በምናደርገው ጉዞ አንድ ሌላ እጥፋት ላይ በመድረሳችን ኢትዮጵያዊያን ሁሉ እንኳን ደስ አለን።

ዛሬ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ እና በዳንጎቴ ግሩፕ መካከል የማዳበሪያ ማምረቻ ኮምፕሌክስ የድርሻ ስምምነት ፈርመናል። 2.5 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት የሚፈስበት ይኽ ሜጋ ፕሮጀክት በአመት እስከ ሶስት ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ማዳበሪያ የሚያመርት ሲሆን ይኽም ኢትዮጵያን ከአለም ግንባር ቀደም አምራቾች አንዷ ያደርጋታል።

ፕሮጀክቱ በሀገር ውስጥ የሥራ እድል ይፈጥራል። ለዘመናት ለተፈተኑት ገበሬዎቻችን አስተማማኝ የማዳበሪያ አቅርቦት ያረጋግጣል። ለምግብ ሉዓላዊነት መንገዳችንም ወሳኝ ርምጃ መውሰዳችንን ያመላክታል። በመላው አኅጉሩ ኢትዮጵያ ያላትን ተወዳዳሪነት በማጠናከር ሕዝባችንን እና ነጋችንን የሚጠቅሙ ስትራቴጂክ ኢንቨስትመንቶችን የመከወን ጽኑ አቋማችንን ያሳያል።

የዛሬውን የፊርማ ስምምነት ተከትሎ ፋብሪካው በሚቆምበት ስፍራ ፕሮጀክቱን በይፋ የምናስጀምር ይሆናል። ይኽን ታሪካዊ ጉዞ ጀምረናል። ለገበሬዎቻችን፣ ለኢኮኖሚያችን እና ለኢትዮጵያ ነገ ስንል እንጨርሰዋለን።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.