
አዲስ አበባ በአለም አደባባይ ሌላኛዋ የኩራታችን ምንጭ !
ባለፉት የለዉጥ አመታት ከተማችን አዲስ አበባን በሁለንተናዊ መልኩ ለነዋሪዎቿ የተመቸች ፣ ለጎብኚዎቿ የተመረጠችና እንደ ስሟ ዉብ አበባ እናደርጋታለን ብለን ከነዋሪዎቻችን ጋር ሌት ተቀን የሰራናቸዉ ስራዎች ይኸዉ ዛሬ ፍሬ አፍርተዉ በአለም አደባባይ አሸናፊ እያደረጉን ይገኛል ።
በተለያዩ መወዳደሪያ መስፈርቶች እየመዘነ እዉቅና እና ደረጃ የሚሰጠዉ የብሉምበርግ ፍላንተሮፒስ ግብረ ሰናይ ድርጅት በከተማችን አዲስ አበባ የነዋሪዎቻችንን የአደጋ ተጋላጭነት ለመቀነስና ለመቆጣጠር በመንገድ ደህንነትና ፍጥነት ማስተዳደር ላይ በአጭር ጊዜ የሰራነዉን ስራና በተጨባጭ ያስመዘገብነዉን ዉጤት በመገምገም በአለም አቀፍ የከተምች የዘርፉ ዉድድር ላይ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ አድርጎናል ።
ይህንን እዉቅናና ክብር የሰጠንን ብሉምበርግ ፍላንተሮፒስን በከተማ አስተዳደራችን ስም ከልብ እያመሰገንኩ በቀጣይም መዲናችንን በሁሉም መመዘኛዎች የተሻለች አለም አቀፍ ተወዳዳሪ እንድትሆን የበለጠ መትጋታችን ይቀጥላል ።
ፈጣሪ ኢትዮዽያንና ሕዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
https://www.facebook.com/share/16zPV6fUL6/?mibextid=wwXIfr
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.