ከንቲባ አዳነች አቤቤ የእግር ኳስ ስፖርትን በከ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ከንቲባ አዳነች አቤቤ የእግር ኳስ ስፖርትን በከተማዋ ይበልጡን ማጠናከር በሚቻልባቸዉ አግባቦች ላይ ፍሬያማ ውይይት አካሄዱ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከኢፌዲሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ እና ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አመራሮች ጋር በመዲናዋ የእግር ኳስ ስፓርትን ይበልጡን ማጠናከር በሚቻልባቸዉ አግባቦች ላይ ፍሬያማ ውይይት አካሄደዋል፡፡ 

በዉይይቱ የኢፌዴሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር  ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ ከለውጡ ወዲህ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአጠቃላይ የስፖርት ዘርፍን ለማጠናከር እያከናወናቸው የሚገኙ ስራዎች አበረታች መሆናቸዉን አንስተዋል፡፡

ለዚህም በ2017 በጀት አመት በአገር አቀፍ ደረጃ አንደኛ በመዉጣት እዉቅና ያሰጠዉ መሆኑን ጠቅሰዉ በተለይም ለታዳጊዎች ለሰጠነዉ ከፍተኛ ትኩረት ምስጋና አቅርበዋል ።

አስተዳደሩ  ለስፖርቱ ዘርፍ እድገት በሰጠው ልዩ ትኩረት 1ሺህ 530 ያህል ደረጃቸውን የጠበቁ የተለያዩ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ተገንብተው ለህብረተሰቡ አገልግሎት እንዲሰጡ አድርጓል። 

እንዲሁም ታዳጊ ስፖርተኞች የሚፈሩባቸው ፕሮጀክቶች እንዲስፋፉ ተደርጓል ፤ በተለይም በሁሉም የስፓርት ዘርፍ ተተኪ ምርጥ ስፖርተኞችን ማፍራት ላይ እየተሰሩ የሚገኙ ተጨባጭ ስራዎች ተጠናክረዉ የሚቀጥሉ ይሆናል።

በዉይይቱ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አመራሮች በመጪዉ 2018 ዓ.ም የስፖርት ዘርፋን ለማጠናከር እና ሰፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ሁሉ ስፓርታዊ ጨዋነትን ተላብሰዉ የታለመላቸዉን አላማ እንዲሳኩ እና በዉጤታማነት እንዲያድግ ስፓርተኞች ፣ የእግር ኳስ ደጋፉዎች ፣ የስፓርቱ ማህበረሰብና ወጣቶች በየአካባቢው ያለዉ አመራር ሁሉም ባለድርሻ አካላት የሚናቸዉን እንዲወጡ በትጋት ለመስራት አቅደዉ ወደ ተግባር መግባታቸዉ አንስተዋል።

ሁሉም ባለድርሻ አካላት ስፖርት ለሰላም ፣ ለፍቅር፣ ለአንድነት፣ ለአገር ግንባታ የሚጫወተው ሚና ላቅ ያለ በመሆኑ ለስራው ልዩ ትኩረት በመሰጠት በትብብር መሰራቱ በስፖርቱ ዘርፍ ላይ በቀጣይም እንደ አገር እመርታዊ ለውጥ ለማምጣት ሚናዉ የጎላ በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል::

ለዚህም ሁሉም ባለድሻ አካላት በቅርርብ ፣ በቅንጅት እና በትብብር የላቀ ስራ ለማከናወን የተጀመሩ ስራዎችን በማጠናከር ኃላፊነትን በአግባቡ መወጣት ፣ ይበልጥ ተቀራርበዉ መስራት እንደሚኖርባቸዉ  ገልፀዋል ።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.