.png)
ከአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን -ጎሮ-ቦሌ አየር መንገድ ቪአይፒ ተርሚናል ያለዉ የኮሪደር ልማት ምን አካቷል?
👉 ኮሪደሩ በሁለተኛ ዙር ከተጀመሩ ስምንቱ ኮሪደሮች አንዱ ነዉ
👉 ከተጠናቁት የኮሪደር ልማት ስራዎች መካከል 4ኛዉ ነዉ
👉 ኮሪደሩ አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማእከልን ከቦሌ ኤርፖርት ቪአይፒ ተርሚናል የሚያገናኝ፣ ከአንበሳ ጋራዥ - ጃክሮስ ጐሮ እና በኮሪደር አንድ ከተሰራው ቦሌ ኤርፖርት መገናኛ ሲኤምሲ ጋር የሚገጥም ነው
👉 የኮሪደሩ አጠቃላይ ስፋት ከ290 ሄክታር በላይ ነዉ
👉 12.74 ኪሎ ሜትር ርዝመት እና 29.446 ኪሜ የሚረዝም የእግረኛ መንገድ አለዉ
👉 15.27 ኪሎ ሜትር የብስክሌት መንገድ፤ ከ550 በላይ ታክሲና ባሶችን የመያዝ አቅም ያላቸው 5 የባስና የታክሲ ተርሚናሎች፤ ከ800 በላይ መኪኖችን የመያዝ አቅም ያላቸው 4 ፓርኪንግን ጨምሮ ታክሲና ባስ መጫኛና ማውረጃ 17 ቤይ ተሰርቶለታል።
👉 5 ኪሎ ሜትር የወንዝ ዳርቻ ልማት እና 2 ድልድዮች እንዲሁም 12 ኪ.ሜ የጎርፍ መውረጃ ቱቦ ዝርጋታን ጨምሮ 3.6 ኪ.ሜ የመጠጥ ውሃ ዝርጋታ እና 669 የመንገድ ዳር መብራቶች ተሰርቶለታል
👉 ትላልቅና መካከለኛ ካፌዎች ፤ 41 መጸዳጃ ቤቶች ፤ 9 የህጻናት መጫወቻ ቦታዎች እና 7 የስፖርት ማዘውተሪያ ሜዳዎችን ጭምሮ 4 ፕላዛዎች እና 130 ሄክታር የሚሸፍን የወንዝ ዳርቻ አረንጓዴ ልማትንም አካቷል
👉 ኮሪደሩ ለነዋሪዎች ሰፊ የስራ እድል የፈጠረ፣ ፅዱ፣ አረንጓዴ እና ምቹ የመኖሪያ አካባቢ የፈጠረ፣ አካታች እና ሁሉንም ሰዉ ከልማቱ ተጠቃሚ የሚያደርግ ነዉ
👉 ከ320 በላይ ህንፃዎች እድሳት በማድረግ እና ከ350 በላይ የንግድ ሱቆች በመክፈት የንግድ እንቅስቃሴው በከፍተኛ ደረጃ እንዲጨምር አድርጓል
👉 የመንገድ መጨናነቅን ችግር በመፍታት የትራንስፓርት ፍሰቱን የሚያቀላጥፍ እና የተለያዩ የአገለግሎት መስጫዎችን ያሻሻለ ውጤታማ ስራ ነው
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.