.png)
ዛሬ በለነገዋ የሴቶች ተሀድሶና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል በተለያዩ ሞያዎች ያሰለጠንናቸውን 810 የ3ኛ ዙር ሰልጣኞች አስመርቀን ወደ ስራ አሰማርተናል።
እንኳን ደስ አላችሁ!!!
ማዕከሉ ለተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች ተጋልጠው ጎዳና የወደቁ፣ ለሴትኛ አዳሪነት የተጋለጡ ሴቶችን ከጎዳና በማንሳት በተለያዩ ክህሎቶች እያሰለጠነ ወደ ስራ እያሰማራ ይገኛል ።
የዛሬውን ጨምሮ ከዚህ ቀደም በተለያዩ ዙሮች አሰልጥነን ወደ ስራ ያሰማራናቸው ሴቶች አጠቃላይ ቁጥር 1692 ደርሷል ።ይህ ስራ ከተማችን ውስጥ ሌት ተቀን ከምንከውናቸው ሌሎች የልማት ስራዎች አልቀን የምናየዉ አንዱና ዋነኛ ስራችን ነው። ሴት እህቶቻችን እነሱ ባልፈጠሩት ችግር ለመራር የህይወት ፈተና ሲጋፈጡ፣ ሲወገዙ፣ ሲገፉ፣ በረንዳ ሲወድቁ፣ ለአስከፊው የሴተኛ አዳሪነት ህይወት ሲጋለጡ ይስተዋላል። የችግሩ ዋነኛ ምንጭ እነሱ ሳይሆኑ በዋናነት ድህነት እና ኋላቀርነት ነው ።
ይህን ችግር ከስሩ የሚነቅለው ብቸኛዉ መንገድ ደግሞ የጀመርነው የኢትዮዽያ ሁለንተናዊ ብልፅግና እውን መሆን ነው። ለዚህም ሌት ተቀን መስራታችን ይቀጥላል ።
የዛሬ ተመራቂ ተማሪዎች ትናንት ከነበሩበት የጎዳና ላይ ህይወት ወጥተው፣ ከአስከፊ ህይወት ተላቀው፣ ከሱስ ተጋላጭነታቸው እና ከጤና ችግሮች ወጥተው በአዲስ ህይወት ጅማሮ ላይ ሆነው በማየታችን እጅግ ደስተኞች ነን።
ተመራቂዎች በቀጣይ ዳግም ላይመለስ በተቀየረው የትላንት ማንነታችሁ ሳትሸማቀቁ ፣ በማዕከሉ ቆይታ ያካበታችሁትን እውቀት፣ ክህሎት፣ መልካም ስነ ምግባር በስራ ላይ እንድታውሉ። በየእለቱ ራሳችሁን በእውቀትና ቴክኖሎጂ ከጊዜዉ ጋር እያሳደጋችሁ ለሌሎች እህቶቻችሁ ምሳሌ እንድትሆኑ አደራ እላለሁ ።
ለዚህ በርካቶችን ከጨለማ ህይወት ታድጎ በቀሪ ህይወታቸው ብርሃን እንዲፈነጥቅ ላደረገ በጎ ስራ በእውቀት፣ በሞያ ፣ በሀብት ድጋፍ ያደረጋችሁ ባለድርሻ አካላት፤ ባለሀብቶች፣ የከተማችን አመራሮች በተለይም አጠቃላይ የተቋሙን አመራሮችና ባለሙያዎች በተመራቂዎቹ ስም እጅግ በጣም አመሰግናለሁ ።
ፈጣሪ ኢትዮዽያንና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/addisababacommunication
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.