ዛሬ የረመዳን ወር ጾምን ምክንያት በማድረግ ከ127 ሺሕ በላይ ለሚሆኑ የከተማችን ነዋሪዎች ማዕድ የማጋራት መርሃ ግብር አስጀምረናል።
በለውጡ መንግስት በጀመርነው የሰው ተኮር ስራችን የህዝባችንን የኑሮ ጫና የማቅለልና አለኝታነታችንን በተግባር የማረጋገጥ በርካታ ስራ በመስራት፣ ማዕድ ብቻ ሳይሆን ለወገኖቻችን ክብር እና ፍቅርን እያጋራን የቆየን ሲሆን በዛሬው ዕለትም ለሁሉም የአዲስ አበባ መስጅዶች የሚከፋፈል ቴምር እና ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ወገኖቻችን ደግሞ ማዕድ አጋርተናል።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.