"በዛሬው ዕለት በከተማችን “በእውቀትና በክህሎት...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

"በዛሬው ዕለት በከተማችን “በእውቀትና በክህሎት የተገነባን ትውልድ መገንባት ለኢትዮዽያ ብልፅግና መሰረት ነው” በሚል መሪ ቃል ለ2 ቀናት የሚቆይ የትምህርት ጉባኤ በይፋ አስጀምረናል ።

በአዲስ አበባ የትምህርት ተደራሽነት እና ጥራትን ለማስጠበቅ በተከናወኑ ተግባራት አበረታች ውጤቶች እየተመዘገቡ ነው።

የትምህርት ዘርፋን ስብራት ለመጠገን በተከናወኑ ተግባራት በዕውቀት እና በክህሎት የታነጸ ትውልድ ለማፍራት የሚያስችሉ ተጨባጭ እርምጃዎች ተወስደው ውጤቶች የተመዘገቡ ይገኛሉ።

መዲናችን በብሔራዊ ፈተና በ8ኛ እና 6ኛ ክፍል ፈተና የተሻለ ውጤት እያስመዘገበች ነዉ ።

እነኚህንና ሌሎችም በርካታ ውጤቶችን በማስመዝገብ ረገድ የመምህራኖቻችን፣ የተማሪ ወላጆች እና የተማሪዎች በአጠቃላይ የትምህርት ማህበረሰብ ሚና ትልቅ ነው።

ይህንን ውጤት የበለጠ ለማላቅና ዘርፉ በትውልድና አገር ግንባታ የሚጠበቅበትን ሚና በአግባቡ እንዲወጣ ፣ ውጤቶች ይበልጥ እንዲልቁ፣ የታዩ ክፍተቶች እንዲታረሙ ይበልጡን ተቀራርቦ መስራት ይገባል ።

ጉባኤው ስኬታማና የታለመለትን ግብ የሚያሳካ እንዲሆን እመኛለሁ "።

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች

https://linktr.ee/addisababacommunication


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.