“ስትሮክ እና ሌሎችም ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

“ስትሮክ እና ሌሎችም ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ስርጭት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ እንደሆነ መረጃዎች ያመላክታሉ ።

ይህንን ችግር አክሞ ለማዳን  የኢትዮዽያ ስትሮክ ፋዉንዴሽን  በመዲናችን የተሟላ የስትሮክ ሕክምና ማዕከል (comprehensive stroke service Center ) ለመገንባት  ላሳዩት ተነሳሽነት ከልብ አመሰግናለሁ።

ማዕከሉ ተገንብቶ ስራ ሲጀምር ከአገር ዉጭ ወጥተዉ መታከም ለማይችሉ ታማሚዎች እና ቤተሰብ ትልቅ እፎይታ የሚሰጥ ሲሆን  በአፍሪካ አህጉር ደረጃ እንኳ በጣም ውስን በሆኑ አገራት ብቻ የሚሰጥ በመሆኑ እንደ አገር ለጀመርነዉ የጤና ቱሪዝምም በዉጭ ምንዛሬ ግኝት የሚኖረዉ ኢኮኖሚያዊ  ፋይዳ  ጉልህ ነዉ ።በመሆኑም የከተማአስተዳደራችን  ለስትሮክ ሕክምና ማዕከል  መገንባት መሬት ከማቅረብ ጀምሮ ሌሎች ድጋፎችን ያደርጋል።

መላዉ የከተማችን ነዋሪዎች ስትሮክን ጨምሮ ሌሎችም ተላላፊ ያልሆኑ ደዌዎችን አስቀድሞ መከላከያዉ መንገድ የአኗኗር ዘይቤ 
 በመሆኑ ለዚህም ታልመዉ በተሰሩ የከተማችን የእግረኛ መንገዶች ፣ የስፓርት ማዕከላት እንድትጠቀሙ እላለዉ”።

ፈጣሪ አምላክ ኢትዮዽያንና ሕዝቦቿን ይባርክ !

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
  https://linktr.ee/addisababacommunication


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.