
“በበዓል ወቅት ሰዉ ሰራሽ የምርት አቅርቦት እጥረትና የዋጋ ንረት እንዳይኖር በትኩረት ይሰራል “ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ከተማ አስተዳደሩ የምርት አቅርቦትን በማሳደግ ሰውሰራሽ የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠር እየሰራ ይገኛል ። አምራቾች በቀጥታ ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያቀርቡ በማድረግ የተሻለ የግብይት ስርዓት መፍጠር መቻሉን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልፀዋል ።
በዛሬዉ እለት የ2018 አዲስ አመት ንግድ ፣ ኤግዚቢሽንና ባዛር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፣ ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ጃንጥራር አባይ እና ሌሎችም ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በአፍሪካ ህብረት የገበያ ማዕከል በይፋ ተጀሞሯል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንዳሉ አበቅርቡ ተመርቀዉ ስራ የጀመሩ የገበያ ማዕከላትም በአል ጠብቀዉ ብቻ ሳይሆን አመቱን ሙሉ በአዘቦት ቀን ጭምር አምራችና ሸማቹን በቋሚነት እንዲያገበያዩ ይደረጋልምና ሸማቾች ላልተገባ የዋጋ ጭማሪ ሳይጋለጡ ወደነዚ ስፍራዎች ጐራዉ ብለዉ እንዲሸምቱ እና አምራቾች በቀጥታ ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያቀርቡ ጥሪ አቅርበዋል።
የበአል ባዛሩ ፣ በአፍሪካ ህብረት ፣ በ4 ኪሎ ችሎት የገበያ ማዕከላት ጨምሮ በሁሉም ክፍለ ከተምች በሚገኙ የገበያ ማዕከላት መካሄድ ጀሞሯል ።
በባዛሩ የተለያዩ የግብርና ፣የኢንዱስትሪ እንዲሁም ለበአል ወቅት የሚያስፈልጉ ሸቀጦች በተመጣጣኝ ዋጋ ለሸማቹ ማህበረሰብ ቀርበዋል ።
በኤዚቢሽንና ባዛሩ መክፈቻ ላይ የተገኙት ጃንጥራር አባይ በበኩላቸው በገበያ ማዕከላቱ ለበአል ብቻ ሳይሆን ሁሌም አምራችና ሸማቹ እንዲገበያይበት ይደረጋል ፣ ሸማቹ ህብረተሰብም በአቅራቢያዉ ወደ ሚገኙ ማዕከላት እየሄደ እንዲገበያይ ጥሪ አቅርበዋል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/addisababacommunication
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.