ከተማ አስተዳድሩ በመስከረም ወር ለሚከበሩ በዓላ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ከተማ አስተዳድሩ በመስከረም ወር ለሚከበሩ በዓላት በቂ ምርት ወደ ከተማዋ ማስገባቱን ቢሮ ገለጿል ::

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ አዲስ ዓመት ያለውን የገበያ አቅርቦትና ቁጥጥርን በሚመለከት ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ሰጥተዋል።

ለ2018 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓል ከማዕከል እስከ ወረዳ የአቅርቦት እና የህገወጥ ንግድ ቁጥጥር ግብረሐይል ተቋቁሞ የቅድመ ዝግጅት ስራ መስራቱን አስታውቀዋል።

በተሰራው የቅድመ ዝግጅት ስራም መንግስት በሚያስተዳድራቸው በ10 የገበያ ማዕከላት፣ በ219 የቅዳሜና እሁድ ገበያዎች እና በ20 ባዛሮች ላይ የተለያዩ ምርቶች በስፋት መግባታቸውን ተናግረዋል።

ለዘንድሮው የአዲስ ዓመት በዓል የቀረበው ምርት ባለፈው ዓመት ከቀረበው ጋር የ25 በመቶ ብልጫ አለው ብለዋል።

በገበያ ማዕከለት የቀረቡት ምርቶች 30 በመቶ ሲሆኑ፤ ቀሪው 70 በመቶ በነጻ ገበያው የሚቀርብ መሆኑን አመላክተዋል።

ከምርት አቅርቦት በተጨማሪም መጋዘን ውስጥ ክምችት እንዳይኖር ክትትልና ቁጥጥር ይደረገል ነው ያሉት።

በህገወጥ ደላላ፣ በዓድ ነገር በሚቀላቅሉ፣ ጊዜ ያለፈባቸው ምርቶችን ወደ ገበያ በሚያስገቡና ዋጋ በሚጨምሩ ነገዴዎች ላይ ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር እንደሚደረግ ጠቁመዋል።

በአጠቃላይ ከተማ አስተዳድሩ በመስከረም ወር ለሚከበሩ በዓላት በቂ ምርት ወደ ከተማዋ ማስገባቱን ቢሮው ገልፆዋል


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.