ልጆቻችን የተሻለች ሀገር እንዲረከቡ እንትጋ -...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ልጆቻችን የተሻለች ሀገር እንዲረከቡ እንትጋ - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ  በአዲስ አበባ ችግኝ የመትከል፣ የኮሪደር ልማት እንዲሁም የወንዝ ዳርቻዎችን የማልማት ሥራ በስፋት መሰራቱንም ተናግረዋል።

በትጋት ሀገራችንን ሠርተን ልጆቻችን የተሻለች ሀገር እንዲረከቡ ማድረግ ከሁላችንም የሚጠበቅ ተግባር መሆን አለበት በማለት አስገንዝበዋል ።

በሁለተኛው ዙር የኮሪደር ልማት እየተከናወኑ ባሉ እና በቀጣይ በሚሠሩ ተግባራት ላይ ገለጻ አድርገዋል።

በገለጻቸውም፤ እያከናወንነው ባለው ተግባር በአፍሪካ የነበረን ከተማ አፍርሶ ልዩ ከተማ የማድረግን ጅማሮ አሳይተንበታል ብለዋል።

የኮሪደር ልማት ሥራው በሁሉም ከተሞች ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል።

ሕዝባችን ለመለወጥ፣ ለማደግ፣ ለመዘመን እና የተሻለ አካባቢ ለመፍጠር የሚከፈለውን ዋጋ ለመክፈል ዝግጁ መሆን አለበት ብለዋል።

በዋዛ ፈዛዛ የምናሳካው ነገር የለም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ደክመን፣ ሠርተን፣ ወጥተን ወርደን ሀገራችንን ሠርተን ልጆቻችን የተሻለች ሀገር እንዲረከቡ ማድረግ ከሁላችንም የሚጠበቅ ተግባር ነው ሲሉ አስግነዝበዋል።

በአዲስ አበባ ችግኝ የመትከል፣ የኮሪደር ልማት እንዲሁም የወንዝ ዳርቻዎችን የማልማት ሥራ በስፋት መሰራቱን ተናግረዋል።

በዚህ አግባብ በሚቀጥሉት ዓመታት ተጨማሪ ሥራዎች ይጠበቁብናል ነው ያሉት።

ከተማ ውስጥ ያሉ የማይገባ ጋዝ የሚያወጡና አየሩን የሚበክሉ መኪናዎችን እንዴት አድርገን እንደምናሻሽል ማሰብና መሥራት ይኖርብናልም ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

ከተማችን ለአገልግሎት፣ ለጎብኚዎች፣ ለፋይናንሺያል ሴክተር የምትመች እና የቴክኖሎጂ ምንጭ መሆን አለባት ሲሉም አብራርተዋል።

ኢንዱስትሪዎች ከከተማ ወጣ ይላሉ፤ ከተማ ውስጥ የምንፈልገው አገልግሎትን፣ ሆቴሎችን፣ የቡና መሸጫዎችን፣ የገበያ ማዕከሎችን እና ሆስፒታሎችን ነው ብለዋል።

በዚህም መሠረት ጎብኚዎች ወደ ከተማ መጥተው ገንዘብ እንዲያፈስሱ ለአገልግሎት የሚሆኑ ጉዳዮችን ማሟላት አለብን ነው ያሉት።

ለኑሮ ምቹ የሆነች፣ ብዙ ገንዘብ የሚንቀሳቀስባት፣ ሰዎች ሠርተው የሚያተርፉባትና ወጥተው የሚገቡባት እንድትሆን የጀመርነውን ሥራ አጠናክረን መቀጠል ይኖርብናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)፤ እስከ አሁን በሠራነው ሥራ ደስተኞች ነን፤ ሕዝባችንም ደስተኛ ነው ብለዋል በገለጻቸው።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.