.png)
"ፅናት-ዘመኑን የዋጀ አርበኝነት" !!
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ጳጉሜ 01/2017 ዓ.ም የጳጉሜን 1 የፅናት ቀን "ፅኑ መሠረት ብርቱ ሀገር" በሚል መሪ ቃል በሃገር አቀፍ ደረጃ በሚከበርበት በዛሬው ዕለት “ፅናት ዘመኑን የዋጀ አርበኝነት" በሚል መሪ ቃል በአድዋ ሙዝየም ሁለገብ አዳራሽ የፓናል ውይይት አካሄደ።
የዕለቱን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ እንደተናገሩት መሪ ቃሉ በጽናት ላይ የተገነባ ሀገር ጠንካራና የማይገበር መሆኑን አፅንኦት እንደሚሰጥና፣ የጽናት ታሪክ የኢትዮጵያውያን የወል ታሪክ መገለጫ ብቻ ሳይሆን ከውስጣዊ ኃይል የሚመነጭ የሉዓላዊነትታችን፣ የአይበገሬነት፣ የእድገት እና የመታደስ ዋስትና ነው ብለዋል።
ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ አክለውም የህዳሴ ግድባችን የፅናት ውጤት በበርካታ ፈተናዎች ውስጥ ጸንቶ ለብሔራዊ ጥቅም የመቆም ውጤት ከመሆኑ ባሻገር ህዳሴ ግድብ ብርሃን ነው ብለዋል።
የሁላችንም ከተማ የሆነችው አዲስ አበባ በሁሉም ረገድ እየተለወጠች እንደመሆኗ መጠን፣ በተለይም በከተማችን 7/24 እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማት ስራ በየዕለቱ አዳዲስ ልማቶችና ፕሮጀክቶች የሚፈጸምባትና የሚታይባት የለውጥ ምሳሌ መሆኗንም ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ገልጸዋል።
የቢሮ ሀላፊዋ አክለውም በሀገር ደረጃ የጀመርናቸው የህዝብ ህይወት ቀያሪ ፕሮጀክቶች እንዲጠናቀቁ፣ የከተማችን አዲስ አበባ እጅግ ፈጣንና ፍትሀዊ የዕድገት ጉዞ በተጀመረበት መንገድ እንዲጓዝ የኛን ጽናት፣ አንድነትና ህብረት በእጅጉ የሚያስፈልግ ስለሆነ የኢትዮጵያን እምርትና ማንሰራራት ከግብ እንዲመታና የብልጽግና ተምሳሌት እንድንሆን በጽናት መቆም አለብን ሲሉ አሳስበዋል።
የፖናል ውይይት መነሻ ሰነድ ያቀረቡት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የኃይማኖት ጉዳዮችና የሰላም ዕሴት ግንባታ ዘርፍ ም/ል ቢሮ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ረታ በገለጻቸውም ፅናት-ሀገር ወዳድነትና ዘመኑን የዋጀ አርበኝነት ምንነት፣ አይነቶች ባህሪያት፣ ብሔራዊ ሀገራዊ ማንነት ማስጠበቅ የሀገር ወዳድነት ዕሴቶችን የሚዳስስ ሰነድ አቅርበዋል።
አቶ ብርሃኑ አክለውም ዜጎች ከሌሎች ወንድሞች ጋር የወል እውነቶች ላይ በጋራ መግባባት የሚያስችል ሁኔታ ላይ መድረስ፣ የሀገር ወዳድነት ፋይዳ ላይ ልብ እና የጋራ ማንነት ላይ ሁሉም መስራት እንዳለበት በሰነዱ አብራርተዋል።
በፖናል ውይይቱም የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊሶ ኮምሽን ጠቅላይ አዛዥ ኮምሽነር ጌቱ አርጋው፣ የአዲስ አበባ ከተማ የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ህብረተሰብ ተሳትፎና የበጎ ፈቃድ ኮምሽን ኮምሽነር አቶ ይመር ከበደ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፤ አባገዳዎች፤ የመከላከያ ሰራዊት አባላት፣ የፌደራል ፖሊስ አባላት፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት፤ የደንብ ማስከበር አባላት የሰላም ሰራዊት እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
የፓናል ውይይቱን የመሩት የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊሶ ኮሚሽን ጠቅላይ አዛዥ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው እና የአዲስ አበባ ከተማ ህብረተሰብ ተሳትፎና የበጎ ፈቃድ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ይመር ከበደ ሲሆኑ በመድረኩ በተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ላይ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል፤
ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው በበኩላቸው በዛሬው ዕለት እየተከበረ ያለውን የፅናት ቀንን ስናስብ ጀግና የመከላከያ ሰራዊታችንንና አጠቃላይ የፀጥታ ሃይሉን እንዲሁም በተደጋጋሚ በሀገራችን ላይ ለነበረው ጦርነት መስዋት የከፈሉትን ሁሉ ማሰብ እንደሚገባ አመላክተዋል፡፡
የውስጥ ጠላቶቻችን ከባንዳዎች ጋር በመሆን በማህበራዊ ሚዲያ የሚያስተላልፉትን ሃገር አፍራሽ መልዕክት አጽንኦት በመስጠት መታገል እንደሚገባ እንዲሁም የሀገራችንን ሰላም፣ ልማት መጠበቅ በዚህ ሁሉ ግን ለሃገር መስዋዕት የሚከፍሉ ጀግኖቻችንን በማሰብ ቀኑን ማክበር እንዳለብን አቶ ይመር ከበደ አሳስበዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.