.png)
ጳጉሜ 2 የህብር ቀን!!
ዛሬ በህብር ቀን ለ500 ሺህ የከተማችን ነዋሪዎችን ማዕድ አጋርተናል።
በክረምቱ ወራትም ምንም ጧሪ፣ ደጋፊ የሌላቸው አቅመ ደካምችን፤ የአገር ባለውለታዎችን እና በዝቀተኛ ገቢ የሚተዳደሩ 156 ሺህ ያህል የህብረተስብ ክፍሎችን ስንደግፍ ቆይተናል።
ወገኖቻችን በጊዜያዊ ችግሮች እንዳይጎዱ በተለያዩ መልኩ ለመደገፍ እየሰራን በዘላቂነት ከድህነት ለመውጣት 24/7 ዘላቂ የልማት ሥራዎችን እየሰራን እንገኛለን።
በመደጋገፍ ፤ በመረዳዳት ለማህበራዊ ችግር ተጋላጮች የምናደርገውን ድጋፍ ማጠናከር ይገባናል። ሁልጊዜ ከጎናችን ሆናችሁ ካላችሁ ለምታካፍሉ፣ ለመስጠት ለማትሳሱ ባለሀብቶች፣ ለከተማችን ወጣቶች ድጋፍ በተደረገላቸው ወገኖቻችን ስሞ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮዽያንና ህዝቦቿን ይባርክ
ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.