ሙህራን በአዲስ አበባ ከተማ እየተገነባ በሚገኘው የኮሪደር ልማት ለከተማዋ ሁለንተናዊ እድገት ከፍተኛ ድርሻ እንደሚኖረው ተናገሩ።
በፓናሉ ውይይት ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር እንደተናገሩት ከተማችንን የማደስ እንደስሟ አዲስ ፣እንደ ስሟ ውብ ከተማ ለማድረግ የሚደረገው ጥረት ፣በታሰበው ጊዜ ግቡን እንዲመታ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የተቀናጀ ርብርብ የሚጠይቅ ነው ብለዋል፡፡
የፓናል ውይይት ላይ ሙሁራንና የዘርፉ ባለሙያዎች ፤የሚመለከታቸው የመንግሥት ተቋማት ተወካዮች ፤የተፎካካሪ ፓርቲ ተወካዮችን ጨምሮ የልማት ተነሺ ተወካዮች ተገኝተው የጋራ አቋም ለመያዝ የሚረዳ የፓናል ውይይት አድርገዋል ።
በፓናል ውይይቱ ላይ ዓለም አቀፍ የከተሞችን ደረጃ የማሻሻል ተሞክሮዎችን ዋቢ በማድረግ ለውይይት መነሻ የሚሆን ጥናታዊ ጽሁፍ ቀረቧል።
በፓናል ውይይቱም ላይ የተገኙት የሲቪል ሙያዎችና የከተማ ማደስ የዕቅድ ስራዎች ረዳት ፕሮፌሰር ዶ/ር ሂርጶ በሬሳ እንደገለጹት :-በታዳጊ አገራት የከተሞችን ገቢ ለማሳደግ ፤የመሰረተ ልማት ዝርጋታን ለማሻሻል ፤ኢንቨስትመንትን ለመሳብ፤የቱሪዝም መዳረሻዎችን ለማስፋትና የቅርሶች ይዞታ ለማሻሻል የሚኖረው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው ብለዋል።
የኮምፓስ የማማከር አገልግሎት ድርጅት ዋና ስ/አስፈፃሚ አቶ ጎሳዬ በቀለ በበኩላቸው የከተማዋን አሁናዊ ተጨባጭ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ በበቂ ጥናት ተግባራዊ የተደረገ መሆኑን የጠቀሱት ወደ ፊት በሚኖረው ውጤትም በኢኮኖሚ፤በስራ እድል ፈጠራ ፤ከምቹ መኖሪያ ግንባታ ፤ውስን የመሬት ሃብትን በአግባቡ በመጠቀም ያስፈልጋል ብለዋል።
የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ኃላፊ ኢ/ር ሞገስ ጥበቡ በፓናል ውይይት መረሀ-ግብሩ ላይ እንደተናገሩት:- አዲስ አበባን በአፍሪካ ተመራጭና ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን የምታሟላ ከተማ እንድትሆን ለማስቻል በቅርቡ የተጀመረውን የኮሪደር ልማት እንቅስቃሴን ጨምሮ በርካታ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ስራዎች በሚፈለገው ፍጥነትና የጥራት ልክ ተግባራዊ እየተደረጉ መሆናቸውን አብራርተዋል ።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.