ለመጪው የኢድአል ፈጥር በዓል ከወዲሁ በቂ ዝግጅት መደረጉን የአዲስ አበባ ከተማ የስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት አስታወቀ።
የአዲስ አበባ ከተማ የስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት ተጠሪ ተቋማት ታላቁ የኢድአል ፈጥር በዓል ያለምንም የኤሌክትሪክ፣የውሃና የመብራት ችግር እንዲሁም የእሳት አደጋ ሳይከሰት እንዲውል ቅድመ ዝግጅት ማድረጋቸውን በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ስ/አስኪያጅ አቶ ተፈራ ሞላ እንደገለጹት ከፊታችን የሚከበረዉ የኢድአል ፈጥር በዓል በሰላምና በደስታ እንዲዉል ስራ አስኪያጅ ቢሮ ከስሩ ያሉትን ተቋማት ለማጠናከር ኮሚቴ አዋቅሮ ወደ ተግባር መግባቱን ተናግረዋል።
በተለይም ከኮሪደር ልማት ጋር ተያይዞ ለሚከሰቱ ማናቸዉም የአገልግሎት መቆራረጥ አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ መሆኑንና የቅድመ መከላከል ስራ ከዚሁ ጋር ተያይዞ እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡
የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ ሃይል አገልግሎት የአዉቶሜሽንና ኢነርጂ ማኔጅመንት ስ/አስኪያጅ ኢ/ር ዘሪሁን አበበ እንደተናገሩት ተቋማችን ከከተማ አስተዳደሩ ጋር የጋራ እቅድ አዘጋጅቶ ከሪጅን እስከ ማእከል በአደረጃጀቶች ወደ ስራ መግባቱንና ከሃይል ማመንጨት ስራ ጎን ለጎን የሀይል መቆራረጥ እንዲቀንስ እየሰሩ እንደሚገኙና ችግር ሲያጋጥም 905 በመደወል አገልግሎት ማግኘት እንደሚቻል ገልፀዋል፡።
የአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ አደጋ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ፍቅሬ ግዛዉ እንደገለጹት ከማእከል እስከ ታችኛዉ መዋቅር በቂ ዝግጅት መደረጉንና የዝናብ ወቅት በመሆኑ በኤሌክትሪክ አጠቃቀም ላይ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ም/ዋ/ዳይሬክተር አቶ ሙላት ተገኝ በበኩላቸው፦ በበዓሉ ወቅት የቆሻሻ ተረፈ ምርት በአይነትና በመጠን ስለሚበዛ ህብረተሰቡ በቂ እና የተደራጁ የሰዉ ሃይል ስላለን እነዚህን አደረጃጀቶች በመጠቀም ቆሻሻን በተገቢዉ ማስወገድ፤እርድን በተገቢዉ ቦታ መጠቀም ይገባል ብለዋል፡፡
በመጨረሻም በጋዜጣዊ መግለጫቸዉ ለሙስሊሙ ማህበረሰብ እንኳን ለ1049ኛ የኢድ አልፈጥር በዓል አደረሳችሁ ብለዋል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.