ዛሬ ማለዳ የከተማችን ነዋሪዎች በነቂስ ወጥተው...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ዛሬ ማለዳ የከተማችን ነዋሪዎች በነቂስ ወጥተው በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ የተመራው ለውጥ 6ኛ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ድጋፋቸውን በሰላማዊ ሰልፍ ገልጸዋል።

ለውጡ ሀገራችንን ከፍ ባደረጉ ታላላቅ ስራዎች እና ህብረ ብሔራዊ ወንድማማችነት ከፍ ብሎ አንድነት የደመቀበት ሲሆን፣ በአዲስ አበባ ደግሞ የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጨምሮ ታላላቅ ፕሮጀክቶችን ጀምረን ያጠናቀቅንበት፣ የቱሪዝም መስህቦች እንዲሁም ማህበራዊ ፍትህን ለማንገስ የጀመርናቸው ለሰው ልጅ ቅድሚያ በሰጠው ሰው ተኮር ስራዎቻችን የበርካቶች የኑሮ ሸክም ቀልሎ እምባቸው ታብሶ ተስፋቸው የለመለመበት ነው።

በቀጣይም መዲናችንን የብልጽግና ተምሳሌት፣ እንደ ስሟ ውብ እና ለኑሮ ምቹ በማድረግ በሁሉም ዘርፍ ዓለም አቀፍ የስበት ማዕከል የማድረግ ጥረታችን ተጠናክሮ ይቀጥላል።

ሁሌም ድጋፋቸው ላልተለየን የከተማችን ነዋሪዎች አክብሮታችን ከፍ ያለ ነው፤ እናመሰግናለን።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.