የረመዳን ፆምና የኢድ አልፈጥር በዓል በእስልምና...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የረመዳን ፆምና የኢድ አልፈጥር በዓል በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ ልዩ ቦታ የሚሰጠው፣ የመረዳዳትና የአብሮነት ምሳሌ ነው""ወይዘሮ_ሂክማ_ከይረዲን

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 1445ኛው የኢድ አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ በዓሉ በሚከበርበት የእስቴዲየም ዙሪያ የፅዳት ዘመቻ አካሄደ።

የፅዳት ተግባሩን ያስጀመሩት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የከተማ አስተዳደሩ ዋና ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ ሂክማ ከይረዲን የታላቁ ረመዳን ፆም በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ ልዩ ቦታ የሚሰጠውና የመረዳዳት ምሳሌ መሆኑን ጠቅሰው የእምነቱ ተከታዮች ይህንን በጎ ተግባር በመፈፀም ከፈጣሪ ዘንድ ታላቅ በረከትን እያገኙበት አሳልፈዋል ብለዋል።

የታላቁ የኢድ አልፈጥር በዓል ከሀይማኖታዊ በዓልነቱ ባሻገር ኢትዮጵያዊነትን የሚያጎላ፣በኢትዮጵያዊነት ገመድ የሚያስተሳስረን ታላቁ እሴታችን ነውም ብለዋል ወይዘሮ ሂክማ ብለዋል።

ወይዘሮ ሂክማ አክለውም እኛ ኢትዮጵያውያን አንድነታችን የጥንካሬያችን መሰረት፣ መተሳሰባችን ያቆራኘን ኢትዮጵያዊ ማሰርያችን፣መከባበራችን የአብሮ መኖራችን ሚስጥርና መለያችን ሆኖ ዘመናትን ተሻግረናል ፤ ትውልዱም ይህንን ድንቅ ጥበብና ሚስጥር ይዞ እንዲቀጥልም እንሰራለን ብለዋል።

በፅዳቱ ላይ የተገኙት የተለያየ እምነት ተከታይ አባቶችና የፅዳት አምባሳደሮችም የእስልምና እምነት የአብሮነትና የኢትዮጵያዊነት መገለጫ መሆኑን ጠቅሰው በዓሉን በትብብርና በአንድነት በማክበርም የነበረውን ኢትዮጵያዊ ትስስራችንን እናስቀጥላለን ብለዋል።

ዛሬ ማክበሪያ ቦታውን እንዳፀዳን ክፋትንና መለያየትን ከውስጣችን ልናፀዳ ይገባል ያሉት የሀይማኖት አባቶቹ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮችም የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.