የሀገራችን ኩራት ከሆነው የኢትዮዽያ አየር መንገ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የሀገራችን ኩራት ከሆነው የኢትዮዽያ አየር መንገድ ግሩፕ ጋር በጋራ በምንሰራባቸው ጉዳዮች ላይ ዛሬ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመናል ። ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ኢትዮጵያውያንን ከዓለም ጋር ከሚያገናኛው  የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሳውን እና ማኔጅመንታቸውን  የወንዝ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማትን ካስጎበኘናቸው በኋላ  በተደራጀ እና በተቀናጀ መልክ በጋራ ለመስራት   የመግባቢያ ሰነድ የተፈራረምን ሲሆን፣ ስምምነቱ በዋናነት በከተማችን የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻዎች ልማት የለሙ አዳዲስ የቱሪዝም  መዳረሻዎችን  የማስተዋወቅ በዚህም  የስቶክ ኦቨር ቱሪዝም ተጠቃሚነትን ማሳደግ፣  የከተማችን አዲስ መለያ የሆነውን new face of Africaን  ማስተዋወቅ፣ የአቪየሽን ደህንነትን ማረጋገጥ፣ በተጨማሪም በከተማው የተለያዩ ማህበራዊና ሰው ተኮር ስራዎችን በጋራ መስራት ላይ ያተኮረ ነው ።
 
አየር መንገዱ በከተማችን በምንሰራቸው ሰው ተኮር የልማት ስራዎች እና በኮሪደር ልማት ላይ ለነበረዉ ድጋፍ ከልብ እያመሰገንን  ፣ የከተማ አስተዳደራችን ለስምምነቶቹ ተፈፃሚነት ከኢትዮዽያ አየር መንገድ ግሩፕ ጋር  ከከዚህ ቀደሙ በበለጠ ተቀራርቦ የሚሰራ ይሆናል ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.