በከተማችን የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥ ስርዓቱ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በከተማችን የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥ ስርዓቱን የጠበቀ እና ቀልጣፋ ለማድረግ የጀመርነውን ስራ አጠናክረን ቀጥለናል።

ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ጋር በመሆን የአዲስ አበባ ከተማን የመሶብ የአንድ መዕከል ዲጂታል የመንግስት አገልግሎትን ስናስጀምር ቅርንጫፎችን  በፍጥነት ለማስፋት በገባነው ቃል መሰረት፣ ዛሬ  12 የከተማ አስተዳደር እንዲሁም 3 የፌደራል ተቋማትን በመያዝ 96 የከተማ አስተዳደር አገልግሎቶች የሚሰጠውን የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ቦሌ ቅርንጫፍን ስራ አስጀምረናል ።

የቦሌ ክፍልከተማ  የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግስት አገልግሎት ስራ ያስጀመርነው  ባለ 6 ወለል ህንፃ በ4 ወራት  ገንብተን፣ አስፈላጊውን ቴክኖሎጂ እና ግብአት አሟልተን  እንዲሁም የሰው ሀይል አሰልጥነን ነው።

ይህንን የአዲስ መሶብ የአንድ መአከል ዲጂታል የመንግስት አገልግሎት በአጭር ጊዜ ግንባታው እንዲጠናቀቅ እና በአስፈላጊው ቴክኖሎጂ እንዲዘምን ለደገፉን  አካላት በሙሉ፣ በተለይም የኢትዮዽያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እና ለከተማችን አመራሮች በተገልጋዩ ህብረተሰብ ስም ከልብ አመሰግናለሁ። ተገልጋዩ ህብረተሰብም በማዕከላቱ በመገኘት አገልግሎቶቹን እንድትጠቀሙ ጥሪዬን አቀርባለሁ ።

ፈጣሪ ኢትዮዽያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.