ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሶስት ወራት በ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሶስት ወራት በፊት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጎብኝተው በገጠር ኮሪደር ልማት ሥራ ሞዴል የገጠር መንደሮችን ጨምሮ አመታዊውን የክረምት በጎ ፈቃድ መርሃ ግብር አስጀምረው ነበር።

በጉብኝታቸው ወቅት የሀምበሪቾ ተራራ 777 ደረጃዎች ወጥተው ለዞኑ አስተዳደር ደረጃዎቹን ጨምረው እንዲገነቡ የቤትሥራ ሰጥተው ነበር። በሶስት ወራት ውስጥ የቤትሥራውን አከናውነው የሀምበሪቾ ተራራ ዳግም 777 ክፍልን እውን አድርገዋል። በድምሩም ከ1500 ደረጃዎች በላይ በማድረስ አስደናቂው የተራራ ላይ እይታ ድረስ ገንብተዋል። 

ለክልሉ ቁርጠኝነት እና ውጤት እውቅና ለመስጠትም ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ከመደመር መንግሥት ሽያጭ የተገኘ ገቢን በሀምበሪቾ ተራራ ሥር የማረፊያ ግንባታ ይገነባ ዘንድ ስጦታ አበርክተዋል። ይኽም አካባቢው በማእከላዊ ኢትዮጵያ ትእይንታዊ ቱሪዝም መዳረሻነት መጎልበት የበለጠ የሚያገለግል ይሆናል።

#PMOEthiopia


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.