ዛሬ በናይሮቢ፣ ኬንያ “ዲጂታላይዜሽንን ለቀጠናዊ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ዛሬ በናይሮቢ፣ ኬንያ “ዲጂታላይዜሽንን ለቀጠናዊ የእሴት ሰንሰለት መጎልበት በመጠቀም ለዘላቂ እና አካታች እድገት ማዋል” በሚል ጭብጥ በተካሄደው 24ኛው የCOMESA መሪዎች ጉባኤ ላይ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን የአፍሪካን የኢኮኖሚ ታሪክ የመቀየር ልዩ እድል እንዳቀረበልን አፅንኦት ሰጥቼ አንስቻለሁ።

እንደ አኅጉር የየሀገሮቻችንን ጥረቶች ለማጣመር እና ቀጠናዊ ትስስሮችን ለማፋጠን ክሂሎቱ እና መሠረቱ አለን።

በኢትዮጵያ ዲጂታል ክሂሎትን ለማበልጸግ እና አስፈላጊ መሠረተ ልማት ለመገንባት ጥሩ ርምጃዎች ተራምደናል። የጋራ ዲጂታል ነጋችንን ለማሳደግ በትብብር ለመሥራት ዝግጁ ነን።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.