3ኛዉ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛመደበኛ ጉባዔዉን እያካሄደ ይገኛል
ምክር ቤቱ 3ኛዉ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛመደበኛ ጉባዔዉን በእድዋ ድል መታሰቢያ በሚገኘዉ የምክር ቤቱ አዳራሽ እያካሄደ ነዉ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባዔ ወ/ሮ ቡዜና አልቃድር በመክፈቻ ንግግራቸዉ እንደተናገሩት 2018 ዓ.ም ህዳሴ ግድብን ያጠናቀቅንበት በርካታ ፕሮጀክት በሩብ ዓመቱ የተጀመሩበት ዓመት በመሆኑ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡
አክለዉም 18ኛዉን የሰንደቅ ዓላማ ቀን እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል፡፡
የዛሬዉ አጀንዳዎችም ፤-የምክር ቤቱን 4ኛ የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባዔ ቃለ ጉባዔ ማፅደቅ፤በከተማዋ ባሉ ክፍለ ከተሞች የተመረጡ የምክር ቤት ዓባላት በበጀት ዓመቱ በ1ኛ ሩብ ዓመት ህዝብ ጋር ወርደዉ በአደረጉት ዉይይት ለቀረቡላቸዉ ጥያቄዎች ለጉባዔዉ በማቅረብ በክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና በሌሎች የምክር ቤት አባላት ምላሽ መስጠት እና ልዩ ልዩ ሹመቶችን ማፅደቅ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በመጨረሻም በቀረበዉ የምክር ቤቱ 4ኛ የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ቃለ ጉባዔ ላይ ምክር ቤቱ ሃሳብ ሰጥቶበት በሙሉ ድምፅ ፀድቆ ጥያቄዎች በምክር ቤት አባላት እየቀረቡ ይገኛሉ፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.