ባለፉት 3 ወራት ከ96 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ወጣቶችና ሴቶች የስራ ዕድል ተፈጥሯል፡፡ አቶ ጥራቱ በየነ
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጥራቱ በየነ ለአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ተመራጭ አባላት በኩል ከመራጩ ህዝብ ለተነሱላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ማብራሪያ ባለፉት 3 ወራት ከ96 ሺህ 200 በላይ ለሚሆኑ ወጣቶችና ሴቶች የስራ ዕድል ተፈጥሮላቸዋል ብለዋል፡፡
የስራ እድል ከተፈጠረላቸው ወጣቶች መካከል 10 በመቶ ለአዳዲስ ምሩቃን እንዲሁም 56 በመቶ ለሴቶች ስራ እድል እንደተፈጠረላቸው አቶ ጥራቱ በየነ ተናግረዋል፡፡
ለኢንተርፕራይዞች በመንግስት የልማት ስራዎችና በኢንዱስርሪዎች የጥሬ እቃ እንዲያቀርቡ በማድረግ የ2 ቢሊዩን የገቢያ ትስስር እንደተፈጠረላቸውም ገልጸዋል፡፡
በተመሳሳይ 996 የመስሪያ ሸዶችን ለአዳዲስ ስራ ፈላጊዎች ማስተላለፍ መቻሉንም እና ሌሎችን በፍጥነት ለማስተላፍ በአመቱ መጨረሻ ለ350 ሺህ ወጣቶች የስራ እድል ለመፍጠር በትኩረት እተሰራ መሆኑንም አቶ ጥራቱ በየነ አስረድተዋል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.