3ተኛዉ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 5ኛ ዓመ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

3ተኛዉ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛመደበኛ ጉባዔ ላይ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡

በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰዉ ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ጀማሉ ጀምበር በሰጡት ማብራሪያ እና ምላሽ እንደገለፁት የአገልግሎት አሰጣጥን በማዘመን የተገልጋዩን እርካታ ለማረጋገጥ ከከተማ አስተዳደሩ ጋር ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡

በከተማችን በቅርቡ ተመርቀዉ ወደስራ የገቡት አዲስ የመሶብ  የአንድ ማዕከል ዲጂታል አገልግሎት ለዚህ ማሳያ ነዉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በዚህ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ሰፊ አገልግሎት እና ሰፊ ተገልጋይ እንዲሁም ቅሬታ የሚበዛባቸዉ ተቋማት በመለየት አደረጃጀትን እና አሰራርን በመዘርጋት እንዲሁም  ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር ወደ ትግበራ መግባት መቻሉን ጠቁመዋል፡፡

በዋና መስሪያ ቤት በአራዳ ክፍለ ከተማ 13 የሚሆኑ የከተማ አስተዳደሩ ተቋማት 107 አገልግሎቶችን በመያዝ የተለዩ የፌደራል ተቋማትን በማካተት እየተሰራ አንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡

በተመሳሳይም በቦሌ ክፍለ ከተማ በአዲስ  የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት 12 የከተማ አስተዳደሩ ተቋማት 96 አገልግሎቶችን እንዲሁም የተለዩ የፌደራል ተቋማትን በማካተት በጥቅሉ 114 አገልግሎቶች እንዲገቡ ተደርጓል፤

በአመለካከት ፣በእዉቀት እና በክህሎት የበቁ ነባርና አዳዲስ ተመረቂ ባለሙያዎችን በማሰልጠንና በመመደብ ፤የቅሬታ አፈታት ስርዓትን በማዘመን ፤ከተቋማት ጋር በቅንጅት በመስራት ይፈጠራሉ ተብለዉ የሚገመቱ ችግሮችን ከወዲሁ ለማረም የተቻለበት ሁኔታ ተፈጥሯል ብለዋል፡፡

በዚህም ከየትኛዉም በኩል የሚመጡ የዜጎች ምልልስ በማስቀረት፤ወጪና ጊዜን በመቆጠብ የተገልጋይን እርካታ ከፍ ማድረግ የተቻለበት ሁኔታ መፈጠሩን  ዶ/ር ጀማሉ ጀምበር ተናግረዋል፡፡ 
 
ይህም ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በሌሎች  ክፍለ ከተሞች ለማስፋፋት እቅድ ተይዞ በልዩ  ትኩረት በቅንጅት እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡

በሌላ በኩልም አዲሱ የደመወዝ ጭማሪ በተመለከተ ለተነሳላቸዉ ጥያቁ ቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸዉና  ክፍያዉ  በቅርቡ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንደሚሆን  አመላክተዋል :: 
 
 ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
  https://linktr.ee/addisababacommunication


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.