ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ የኑሮ ውድነት ጫና ለማቃለል የሚደረገውን ብርቱ ጥረት በተመለከተ የሰጡት ማብራሪያ
👉በበዓላት ወቅት የሚፈጠሩ የዋጋ ውድነቶችን ለመከላከል አቅደን ሰርተናል።
👉በታላላቅ የገበያ ማዕከላት የምርት እጥረት እንዳይኖር ተሰርቷል።
👉በክቡር ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ አቅጣጫ መሰረት ምርቶች ከሁለም ክፍሎች እንዲገቡ ከማህበራት በጋራ እየተሰራ ነው።
👉የንግድ ኮርፖሬሽንን የማጠናከር ስራ ተሰርቷል። የእሁዱ ገበያ እና የምገባ ማዕከላትን ማጠናከር ስራ ተከናውኗል። 500 ሺህ ለሚሆኑ ነዋሪዎችም የማዕድ ማጋራት ስራ ባለሀብቶችን በማሳተፍ ተከናውኗል። የዳቦ ዋጋንም በመደጎም ለህዝባችን ማሻሻል ተችሏል።
👉የእሁድ ገበያን ለማጠናከርም ብርቱ ስራዎች ተሰርተዋል ፤ ክፍተቶች እንዲታረሙ ይሰራል።
👉የጤና መድህን ፣ ትራንስፖርት ወዘተ 14 ቢሊዮን ብር የድጎማ በጀት ተይዞ እየተሰራ ሲሆን በዋንኛነት ግን የህዝባችንን ህይወት በዘላቂነት ለማሻሻል እየተሰራ ነው፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.